በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአፋር ክልል የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ


አፋር አብአላና አካባቢ
አፋር አብአላና አካባቢ

የህወሓት ታጣቂዎች በአፋር አብአላና አካባቢው አጠናክረው በቀጠሉት ጥቃት ምክንያት የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አስተየታቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

"ተፈናቃዮችን ይዘው በመንቀሳቀስ ላይ በነበሩ ሦስት ተሸከርካሪዎች ላይ የህወሓት ኃይሎች ሰነዘሯቸው በተባለ ጥቃትም የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል" ሲሉ በአካባቢው ነዋሪ መሆናቸውን የገለፁ ግለሰብ ተናግረዋል።

ተፈናቃዮቹ የሚገኙበት ሁኔታም አሳሳቢ በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን እገዛ እንዲያደርግላቸው ጠይቀዋል።

ህወሓት ዛሬ አወጣው በተባለና አሁን ማምሻውን በደረሰን መግለጫ፤ በአፋር ክልል ፕሬዚዳንት ልዩ ፖሊስና በኤርትራ መንግሥት ይደገፋል ባለው፤ “የቀይ ባህር አፋር ኃይል”ላይ ከትናንት ማለዳ ጀምሮ ጥቃት መክፈቱን አስታውቋል።

ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ከአፋር ክልል የሚፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:18 0:00


XS
SM
MD
LG