አዲስ አበባ —
የዩናይትድ ስቴትስ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና አዲሱ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዛሬ ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር አዲስ አበባ ላይ እንደሚነጋገሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ጠቁመዋል።
35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በመጭው ሣምንት አዲስ አበባ ውስጥ መካሄድ መቻሉ ለኢትዮጵያ ትልቅ ዲፕሎማሲያዊ ድል እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የአፍሪካ መሪዎች አዲስ አበባ ላይ ለመገናኘት መወሰን “ሰላም የለም” የሚለውን ንትርክ ያፈርሳል” ብለዋል ዲና ሙፍቲ።