በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጠ/ሚ ዐቢይ ድምፃዊ አሊ ቢራን በሆስፒታል ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል በመገኘት በሕክምና ላይ የሚገኘውን አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራን በጠየቁ ወቅት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ፣ የኦሮምያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአዳማ ጄኔራል ሆስፒታል በመገኘት በሕክምና ላይ የሚገኘውን አርቲስት ክቡር ዶ/ር አሊ ቢራን በጠየቁ ወቅት

ጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ በሕክምና ላይ የሚገኘውን ታላቁን አንጋፋ ድምፃዊ አሊ ቢራን በሆስፒታል በመገኘት በዛሬው ዕለት ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ አንጋፋዉን ድምፃዊ የጠየቁት ሕክምና እየተከታተለ ወደሚገኝበት የአዳማ ጄነራል ሆስፒታል በማምራት ነው።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መገኘታቸውን ተመልክቷል፡፡

እጅግ ዝነኛ ከሆኑ ቀደምት ኢትዮጵያዊ ድምፃዊያን አንዱ የሆነው አሊ ቢራ በተለይም ዘመን በማይሽራቸዉ የአፋን ኦሮሞ ሙዚቃዎቹ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG