በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማንሽን የባይደንን የ2.5 ትሪሊዮን ዶላር ማህበራዊ ደህንነት በጀት ተቃወሙ


የዌስት ቨርጂኒያው ሴነተር ጆ ማንሽን
የዌስት ቨርጂኒያው ሴነተር ጆ ማንሽን

ከዴሞክራቲክ ፓርቲ የህግ መወሰኛም ምክር ቤት አባላት መካከል መካከለኛውን አቋም የያዙ ናቸው የሚባሉት የዌስት ቨርጂኒያው ሴነተር ጆ ማንሽን ወደ 2 ትሪሊዮን ዶላር የሚጠጋውን የፕሬዚዳንት ባይደን የማህበራዊ ደህንነት ሴፍቲኔት የወጭ እቅድ እንደሚቃወሙ አስታውቀዋል፡፡

ይህ እቅዱ የሚሸፍናቸውና የሚያስወጣቸው ወጭዎች ጠንካራ ክለሳ እንዲደረግባቸው ሊያደርግ ስለሚችል የማለፍ እድሉን ያጨልመዋል ሲሉ ባለሙያዎች ያላቸውን ስጋት ገልጠዋል፡፡

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አሁንም እንደገና ሴነተሩ ሀሳባቸውን ይለውጡ እንደሆነና መጀመሪያ የገቡትን ቃል እንዲጠብቁ መጎትጎታችንን እቀጥላለን ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG