አዲስ አበባ —
በሀገር አቀፍ ደረጃ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለአንድ ሳምንት ተዘግተው፣ ተማሪዎቹ እና መምህራን ለጦር ዘማቾች ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን እንዲሰጡ ተወሰነ።
ይህም ተማሪዎች ከጦርነቱ በኋላ ሀገር በመገንባት ሂደት ለሚኖራቸው ተሳትፎ ልምድ የሚያገኙበት እና ቃል የሚገቡበት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ገልጸዋል፡፡
በሌላ ዜና ከትግራይ ክልል ውጭ፣ በአማራ ክልል ጦርነቱ በተስፋፋባቸው አካባቢዎች፣ ከ 1,600 በላይ መደበኛ የትምህርት ተቋማት ለጉዳት መዳረጋቸውን እና ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት መራቃቸውንም የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ገልጸዋል፡፡
ለችግር በተጋለጡ ሰባት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት በሌሎች ተቋማት የመመደቡ ሥራ ይቀጥላልም ብለዋል፡፡