ድሬዳዋ —
ኢትዮጵያ ከአጎራባች ሃገሮች ጋር ያላትን የድንበር ፀጥታ ለማረጋገጥ ከሃገሮቹ ጋር እየሠራ መሆኑን የሶማሌ ክልል መንግሥት አስታውቋል።
ከኬንያ፣ ከሶማልያ፣ ከጂቡቲና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ከሌላት ሶማሊላንድ ጋር ድንበር የሚጋራው የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር መስጠፋ ኡመርና ምክትላቸው ሰሞኑን ወደ ሃገሮቹ ተጉዘው በዚሁ የድንበር ፀጥታ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።
የድንበሩን ፀጥታ በክልሉ ልዩ ኃይል እያስጠበቀ መሆኑንም ገልጿል።
የፕሬዝዳንት ሙስጠፌ ጉብኝት ምጣኔ ኃብታዊ ተልዕኮም የነበረው መሆኑ ተነግሯል።
/ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።/