አዲስ አበባ —
በአዲስ አበባ የሚገኙ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አባላት ስለ ደህንነታቸው ለከተማ አስተዳደሩ ጥያቄ አንስተው ምላሽ እንደተሰጣቸው ተገለጸ።
የከተማ አስተዳደሩ ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ከተማ ላደረጉ የአፍሪካ፣ የኤዢያና ፓስፊክ ሀገራት አምባሳደሮች እና ሌሎች የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት፣ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ አድርጓል፡፡ ዲፕሎማቶቹ በዚህ ወቅት ደህንነታቸውን በተመለከተ ጥያቄ አንስተው ስለተሰጣቸው ምላሽ፣ ውይይቱን የተከታተሉት የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ ለአሜሪካ ድምጽ አብራርተዋል፡፡
የሰሜን ኢትዮጵያው ግጭት መስፋፋቱን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎች አንዳንድ ሀገራት፣ ዲፕሎማቶቻቸውን ጨምሮ ዜጎቻቸውን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት እንቅስቃሴ መጀመራቸው ይታወሳል፡፡ //ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የምስል ፋይል ያዳምጡ//