በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦባሳንጆ የድርድር ተስፋ ቢኖርም ያለተኩስ ማቆም አይሆንም አሉ


ፎቶ ፋይል-በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሲጉን ኦባሳንጆ
ፎቶ ፋይል-በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሲጉን ኦባሳንጆ

በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሲጉን ኦባሳንጆ ትናንት እሁድ ባወጡት መግለጫ ለአንድ ዓመት የዘለቀው የኢትዮጵያው ግጭት በሰላማዊ ድርድር እንደሚፈታ አሁንም ተስፋ ያላቸው መሆኑን ገልጸው፣ ይሁን እንጂ ድርድሩ ያለ አስቸኳይ ተኩስ ማቆም፣ ተግባራዊ ሊደረግ እንደማይችል አስጠንቅቀዋል ሲል አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሞቱበትና በሚሊዮን ሰዎች የተፈናቀሉበት ጦርነት እንዲያበቃ፣ ዓለም አቀፍ ሽምግልናውን ሲመሩ የቆዩት፣፣ የቀደሞ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት ኦባሳንጆ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ውጊያው እየተባባሰ መምጣቱን በመጥቀስ፣ በእንዲህ ያለ የጦርነት ሁኔታ ውስጥ ንግግሮች ውጤት ሊሰጡ አይችሉም ብለዋል፡፡

ሁሉም ወገኖች ወታደራዊ ጥቃቱን በአስቸኳያ እንዲያቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ እና ከትግራይ ኃይሎች አመራር ጋር የተገናኙት ኦቦሳንጆ ባለፈው ሀሙስ ኢትዮጵያን ለቀው የወጡ ሲሆን በአዲስ አበባ የዲፕሎማሲው እንቅቃሴ መፋጠኑ ተነግሯል፡፡

የዩናይትድ ስትቴስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ ልኡክ ጀፍሪ ፊልትማን ባላፈው ሳምንት ለውይይት አዲስ አበባ መግባታቸው ሲነገር የኬኒያው መሪ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታም ባልተጠበቀ ጉብኘት ትናንት እሁድ በኢትዮጵያ ተከስተዋል፡፡

ሰሞኑን በሦስት የአፍሪካ አገሮች ጉብኝት የሚያደርግኡት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከንም የኦቦሳንጆን ጥሪ እንደሚደግፉት አስታውቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG