በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ አነስተኛ መሆኑ ተገለፀ


የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ከአማራ ክልልርዕሰ መስተዳድር  እና ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ ድጋፍ  አቅርቦት ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ መክረዋል
የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ከአማራ ክልልርዕሰ መስተዳድር  እና ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ ድጋፍ  አቅርቦት ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ መክረዋል

በአማራ ክልል በጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ዜጎች የተደረገው ድጋፍ አነስተኛ መሆኑን በተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶክተር ካትሪን ሱዚ ገለፁ። ዶክተር ካትሪን ለድጋፉ አነስተኛ መሆን የጦርነቱን ሂደት መራዘም፣ የተጎጂዎች ቁጥር በየጊዜው መጨመርና ንፁኃን የጦርነቱ ሰለባ መሆናቸውን በምክንያትነት ጠቅሰዋል፡፡

በቀጣይም ችግሮችን ተቋቁመው የህይወት አድን ሥራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ጦርነት ከ1.9 ሚልየን ዜጎች መፈናቀላቸው፤ ከ6ሚልየን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው እንዲሁም ሰዎች በርሃብ እየሞቱ መሆኑን የክልሉ መንግሥት ገልጿል፡፡

የተለያዩ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ድርጅቶች ከአማራ ክልልርዕሰ መስተዳድር እና ከክልሉ ባለስልጣናት ጋር በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ዙሪያ በባህር ዳር ከተማ መክረዋል፡፡

በሌላ በኩል የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ረዳት ዋና ጸሐፊ ማርቲን ግሪፊትስ ትናንት መቀሌን ጎብኝተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

ከአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚደረገው ድጋፍ አነስተኛ መሆኑ ተገለፀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:16 0:00


XS
SM
MD
LG