በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ88 ዓመቱ የካሜሩን ፕሬዚዳንት በ2025 ምርጫ ይወዳደራሉ?


ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ (ፎቶ ፋይል)
ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ (ፎቶ ፋይል)

ካሜሩንን ለ39 ዓመታት የመሩት የ88 ዓመቱ አዛውንት ፕሬዚዳንት ፖል ቢያ የ7 ዓመት የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ሲያልቅ እኤአ በ2025 ለሚጀምረው ሌላ የ7 ዓመት የሥልጣን ዘመን ካሜሩንን ለመምራት ፡በዝግጅት ላይ ናቸው መሆናቸውን ደጋፊዎቻቸው ተናገሩ፡፡

ፕሬዚዳንት ቢያ ወደ ሥልጣን የመጡት እኤአ በ1982 ሲሆን ከዚያ በፊትም ለ8 ዓመታት ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ካሜሩንን መርተዋል፡፡

ሥልጣን እንደያዙ ያደረጉት የመጀመሪያው ነገር የመሪዎችን የሥልጣን ዘመን የሚገድበውን ህገመንግሥት መለወጥ እንደሆነም ተመልክቷል፡፡

እኤአ በ2018 በተደረገው የካሜሩን ምርጫ፣ በ80 ከመቶ ማሸነፋቸውን ያወጁት የ88 ዓመት እድሜ ባለጸጋው ቢያ ፣ ለረጀም ጊዜ ሥልጣን ላይ በመቆየት ከአፍሪካ ሁለተኛው መሪ ናቸው፡፡

ቀዳሚው እኤአ ከ1979 ጀምሮ ለ42 ዓመታት ሥልጣን ላይ ያሉት በአፍሪካ የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዚዳንት ኦቢያንግ ኑጉዬማ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡

የካሜሩን ገዥ ፓርቲ የካሜሩን ህዝብ ዴሞክራቲክ ንቅናቄ ፓርቲ የ88 እድሜው ባለጸጋ ከዛሬ አራት ዓመት በኋላ ለሚደረገው ሌላኛው የ7 ዓመት የሥልጣን ዘመን ዝግጁ መሆናቸውን እየቀሰቀሱ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን ይህ ተቀባይነት የሌለው ቀድል ነው በማለት ተቃውሟቸውን እያሰሙ መሆኑን የቪኦኤ ዘጋቢ ሞኪ ኤድዊን ከካሜሩን የላከው ዘገባው አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG