በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ያለ ቅድመ ሁኔታ በኢትዮጵያ ድርድር እንዲደረግ ጠይቃለች


ዘጠኝ የሚሆኑ ፀረ መንግሥት ድርጅቶች ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከህወሃት ጋር መጣመራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ፎቶ/ኤፒ
ዘጠኝ የሚሆኑ ፀረ መንግሥት ድርጅቶች ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከህወሃት ጋር መጣመራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። ፎቶ/ኤፒ

ዘጠኝ የሚሆኑ ፀረ መንግሥት ድርጅቶች ከህወሃት ጋር መጣመራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

ዩናይትድ ስቴትስ ህወሃት ደሴንና ኮምቦልቻ ከተሞችን መቆጣጠሩ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ ሊያራዝመው ይችላል በሚል እንዳሳሰባት ገልፃለች።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኑ ብሊንከን ዛሬ በትዊተር ላይ ባሰፈሩት መልዕክታቸው፤ በጦርነቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጦርነቱን አቁመው ለድርድር እንዲቀርቡም ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ አፍሪካዊያን መሪዎችም የኢትዮጵያ መንግሥት በአሸባሪነት የፈረጀው ህወሃት ራሳቸውን የትግራይ ኃይሎች በማለት የሚጠሩት ታጣቂዎች፤ “ወደ ዋና ከተማው እየገሰገስን ነው” ማለታቸው ከተሰማ በኋላ በአቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግና በጦርነቱ እየተሳተፉ ያሉ አካላት በሙሉ ለድርድረ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዘጠኝ የሚሆኑ ጸረ- መንግሥት ቡድኖች ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ዛሬ ከህወሃት ጋራ በመሆን መንግሥትን ለመጣል ጥምረት እንመሰርታለን ማለታቸውን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ የተጠየቁት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ቃል አቀባይ ቢልለኔ ስዩም ሮይተርስ ከዚህ ቀደም በትዊተር ገጻቸው ላይ ያሰፈሩትን እንደምላሽ እንዲጠቀም መግለጻቸው ጠቅሷል።

በተባለው የቢልለኔ የትዊተር ገፅ ላይ የሰፈረው ጹሑፋቸው፤ "ከሦስት ዓመታት በፊት የተከፈተው የፖለቲካ ምህዳር ለተቀናቃኞች ልዩነታቸውን በምርጫ ኮሮጆ በሰኔ 2013 ዓ.ም እንዲፈቱ ዕድል ፈጥሯል" ይላል።

በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት አምንሰቲ ኢንተርናሽናልም በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በኢትዮጵያዊያን ዘንድ የብሄር ግጭት የሚቀሰቅሱ የጥላቻ ንግግሮች መጨመራቸው እንዳሳሰብው ገልጿል።

//የአምነስቲን መግለጫ፣የሮይተርስን ዘገባ ሌሎች ተያያዥ መግለጫዎችን ተካተውበት የተጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ//

ዩናይትድ ስቴትስ ያለ ቅድመ ሁኔታ በኢትዮጵያ ድርድር እንዲደረግ ጠይቃለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:44 0:00


XS
SM
MD
LG