በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ኮቪድ 19 ከትባት ውጤታማነት ከፍተኛ ነው” ተባለ


አንድ ጊዜ የሚሰጠው የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን የኮቪድ 19 ክትባት መድሃኒት ቫይረሱን በመቋቋሙ ረገድ ወደ 74 በመቶ ውጤታማ መሆኑን ትናንት በጃማ ኔትዎርክ ኦፕን የሳይንስ መጽሄት ላይ ታትሞ የወጣ “የሪል ዎርልድ ስተዲ” ጥናታዊ ዘገባ አመለከተ፡፡

ውጤቱ የተገለጸው፣ በሚኒሶታ እውቁ የማዮ ክሊኒክ ተመራማሪዎች በዚህ ዓመት፣ ከየካቲት እስከ ሀምሌ ክትትል ካደረጉባቸው 90ሺ በሚደርሱ ህሙማን ውስጥ፣ 9ሺ ለሚሆኑ ሰዎች፣ የጆንሰን ኤንድ ጆንሰን ክትባት በመስጠት ነው፡፡

ከዚያ ውስጥ ክትባቱን ከወሰዱት 60 የሚሆኑ ሰዎች ብቻ የኮቪድ 19 ቫይረስ የተጋለጡ መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፣ ክትባቱን ካልወሰዱ 88ሺ 898 ሰዎች መካከል 2ሺ 236 የሚሆኑት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

ቻይና ዜጎችዋ መሠረታዊ ፍጆታን እንዲያከማቹ መከረች ቻይና አሁን ድረስ ከቀጠለው ከኮቪድ 19 ቀውስ ጋር እየታገለች በመሆኑ፣ ቻይናውያን ቤተሰቦች የእለት መሠረታዊ ፍጆታቸውን እንዲቆጥቡና እንዲያከማቹ የቻይና የንግድ ሚኒስቴር መመሪያ ሰጠ፡፡

ቤጂንግ እኤአ በ2019 ውሃን ቻይና መከሰት የተጀመረውን ፣ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል፣ ስፋት ባለው አካባቢ በአንድ ጊዜ ምርመራ ማድረግና ጥብቅ ክትትልና እምርጃ የሚያስወስድ የዚሮ ኮቪድ ፖሊሲ ትከተላለች፡፡

ይሁን እንጂ ከወረርሽኝ በተጨማሪ በቅርቡ በተከሰተው አደገኛው የአየር ጠባይ፣ ከመጠን በላይ እየተወደደ የመጣ የአትክልት ዋጋ እየታየባት መሆኑንም ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG