በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ለዜጎች የጉዞ ማሳሰቢያ አወጣ


በኢትዮጵያ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የጸጥታ ሁኔታ በተለይ ባለፉት ቀናት ውስጥ በተለይ በአማራ፣ በአፋርና ትግራይ ውስጥ እየተባባሰ በሄደው የትጥቅ ግጭት የሰላማዊ ዜጎች አለመረጋጋት እየጨመረ በመምጣቱ፣ ወደ ኢትዮጵያ ለመጓዝ ያሰቡና፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ፣ የዩናትድ ስቴትስ ዜጎች በጥብቅ እንዲያጤኑት መክሯል።

“አዲስ አበባን ከሰሜን ከተሞች ጋር የሚያገናኙ መንገዶች፣ በፌደራል መንግሥቱ የተገደቡ ሆነዋል፣ በአካባቢው የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ስለተገቱ መንገደኞችም መንቀሳቀስ አልቻሉም” ያለው ኤምባሲው

“በአጠቃላይ አካባቢው መንቀሳቀስ የማይቻልበት ሆኗል፡፡” ብሏል፡፡

መግለጫው “የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሠራተኞች፣ በአሁኑ ወቅት፣ ከአዲስ አበባ የከተማ ክልል ውጭ እንዳይጓዙ ተከልክለዋል፡፡” በማለት ያለውን ሁኔታ አመልክቷል፡፡

ስለዚህ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት የሚፈልጉ፣ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎችም ሆኑ፣ አሁን በኢትዮጵያ የሚገኙ፣ አገሪቱን ለቀው ለመውጣት ስለሚችሉበት ሁኔታ ቢያስቡበትና ቢዘጋጁበት “በጥብቅ እንደሚመክርም” የኤምባሲው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በመጨረሻም “በኢትዮጵያ የትምገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ ከሆናችሁ፣ ወይም የዩናይትድ ስቴትስ ዜጋ የሆነ የቤተሰብ አባል ካላችሁ፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የምትኖሩም “በአስቸኳይ AddisACS@state.gov” በሚለው አድራሻ አግኙን” ሲል ኤምባሲው መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በመጨረሻም የሚመለከታቸው ሁሉ “እንደ አውሮፓውያን የቀን አቆጣጠር መስከረም 16/2021 ወደ ኢትዮጵያ ለመሄድ ለሚያስቡ የዩናይትድ ስቴትስ ዜጎች የወጣውን የጉዞ ምክር እንዲመለከቱ” በተጨማሪነት ጋብዟል፡፡

XS
SM
MD
LG