በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዋግ ህምራ በምግብ እጥረት ሰዎች እየሞቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ


በዋግ ህምራ በምግብ እጥረት ሰዎች እየሞቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:34 0:00

በዋግ ህምራ በምግብ እጥረት ሰዎች እየሞቱ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ

በዋግ ህምራ ዞን በህወሃት ቁጥጥር ሥር በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ “በረሃብ ምክንያት ብዙ ሰው እየሞተ ነው” ሲሉ የጋዘ ጊብላ ወረዳ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰሎሞን መዓዛ ዛሬ ለአሜሪካ ድምፅ ገልፀዋል።

ወረዳው በህወሃት ቁጥጥር ሥር ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ቅርብ ቀን ድረስ በቦታው እንደነበሩ የተናገሩት አቶ ሰሎሞን “ከዚህ ቀደም በእርዳታ ይኖሩ የነበሩና አካባቢያቸውን ለቅቀው መውጣት ያልቻሉ አቅመ ደካሞች በየቀበሌው እየሞቱ ነው” ብለዋል።

ሰብዓዊ እርዳታ የሚያቀርቡ ድርጅቶችም እስካሁን ወደ አካባቢው አለመግባታቸው ችግሩን እንዳባባሰው አቶ ሰሎሞን አክለው ገልፀዋል።

ከወረዳው አካባቢዎች ትናንት የወጡ 12 ወጣቶች በዞኑ ውስጥ አስከፊ ረሃብ መከሰቱን ይናገራሉ።

ሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች ከጦርነቱ በኋላ ወደ ዋግ ህምራ ገብተው እንደማያውቁ የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትናና ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካባቢዎች ጉዳዮች ኮሚሽነር አቶ እያሱ መስፍን ገልዋል።

ቀደም ሲል አሥር ሰው መሞቱ በመገናኛ ብዙኃን የተገለፀ ቢሆንም ቁጥሩ በብዙ እጥፍ እንደሚጨምር ከየአካባቢው በየቀኑ የሚፈናቀሉ እንደሚነግሯቸው ኮሚሽነሩ አክለው አመልከተዋል።

XS
SM
MD
LG