ድሬዳዋ —
በድሬዳዋና በሐረማያ መካከል ተራራማና ረባዳ መሬት ከሚገናኙበት ቦታ ጀምሮ እስከ አፋር ድረስ ባለው የስምጥ ሸለቆ አካባቢ በአንድ ሳምንት ውስጥ አራት ግዜ ርዕደ ምድር መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲው ፕሮፌሰር አታላይ አየለ አረጋግጠዋል።
ከፍተኛ መጠን ያለውና በሬክተር ስኬል 4.5 መጠን የተመዘገበ ርዕደ ምድር መከሰቱን የገለፁት ፕሮፌሰር አታላይ ንዝርቱ ድሬዳዋና ሐረር ከተማ ድረስ መሰማቱን ተናግረዋል። አራቱ የተሰሙት ብቻ እንደሆነ ጠቁመው በአጠቃላይ አሥር ይሆናሉ ብለዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡