በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጋር የወገኑ ሰልፈኞች ቤተመንግሥቱ ደጅ ላይ ተሰብስበው ውለዋል


ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጋር የወገኑ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ትናንት ለሦስተኛ ቀን ቤተመንግሥቱ ደጅ ላይ ቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 6/2013 ዓ.ም ተሰብስበው ውለዋል።
ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጋር የወገኑ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ትናንት ለሦስተኛ ቀን ቤተመንግሥቱ ደጅ ላይ ቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 6/2013 ዓ.ም ተሰብስበው ውለዋል።

ከሱዳን ወታደራዊ መሪዎች ጋር የወገኑ በሺሆች የሚቆጠሩ ሰልፈኞች ትናንት ለሦስተኛ ቀን ቤተመንግሥቱ ደጅ ላይ ተሰብስበው ውለዋል።

ይህ ከለት ወደለት እያደገ የመጣ ቀውስ በሲቪሎች የሚመራውን ጊዜያዊ መንግሥት ለውድቀት እንዳይዳርገው ተንታኞች እያስጠነቀቁ ነው።

“አንድ ህዝብ፣ አንድ ጦር” የሚል መፈክር እያሰሙ ከቅዳሜ አንስተው በቤተመንግሥቱ ደጅ የተቀመጡት ተቃዋሚዎች ጥያቄዎቻቸው ሳይመለሱ ተነስተው እንደማይሄዱ ሲናገሩ ቆይተዋል። እንዲያውም ድንኳን እየደኮኑ ሌት ተቀን እዚያው ውለው ማደርን መርጠዋል።

ጥያቄዎቻቸው ከምጣኔ ኃብት እስከ እስከ ፖለቲካ ጥያቄ የተዘረጉ ሲሆኑ “የትም በማያደርሱን የቀድሞ አስተዳደር ፖሊሲዎች የሚመሩ ጥቂት ፓርቲዎች የሃገሪቱን ዕጣ ለመወሰን እየተንቀሳቀሱ ነው፤ ሰዉ የሚበላ እያጣ፣ ህይወት ለሁሉም እየከበደች ነው” የሚሉ ቅሬታዎችና መንግሥቱ በአስቸኳይ ተበትኖ በሰለጠኑ ባለሙያዎች እንዲተካ የሚጠይቁ ናቸው።

አንዳንድ ተቃዋሚዎች ደግሞ “’የነፃነትና የለውጥ ኃይሎች’ በሚባለው ቅንጅት ውስጥ የታቀፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች እራሳቸውን ከሃገሪቱ የፖለቲካ ሂደት ነጥለዋል፤ የሱዳን አብዮተኞች ህይወት የከፈሉላቸውን ግቦች ለማሳካት የሚያስችል የሚረባ ተግባር እያከናወኑ አይደሉም” ሲሉ ይከስሳሉ።

ከተቃዋሚዎቹ መካከል ሙህዲን አዳም የሚባሉ የሱዳን ነፃነት ንቅናቄ አባል ለቪኦኤ የደቡብ ሱዳን ፕሮጀክት በሰጡት ቃል “ሰዉ ታክቶታል፤ ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲና ብልፅግና መዝለቅ ይፈልጋል” ብለዋል።

በሌላ በኩል የጊዜያዊው መንግሥት ደጋፊዎች ከነዚህን የሰሞኑ ተቃውሞዎች ጀርባ ያሉትና የሚያንቀሳቅሷቸው “ፀረ አብዮተኞችንና የአል በሽር አፍቃሪዎችን ያቀፉ የጦሩ አባላትና የሃገሪቱ የፀጥታ ኃይሎች ናቸው” ሲሉ ይከስሳሉ።

የፕሬዚዳንት አል በሺር መንግሥት የዛሬ ሁለት ዓመት ከተወገደና ጊዜያዊ መንግሥቱ ከተቋቋመ ወዲህ ሱዳን እጅግ ከባድ የሚባል የውጥረት ጊዜ ላይ የምትገኝ ሲሆን በተለይ ባለፈው ወር ከተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ በኋላ የአል በሺር ታማኞች በሲቪሉ ካቢኔና በውርግርጉ ጥምር መንግሥት ውስጥ ለውጦች እንዲካሄዱ ግፊታቸውን እያጠናከሩ መሆናቸው ተዘግቧል።

ተቀማጭነታቸውን ኻርቱም የሆነው የፖለቲካ ተንታኝ ሃሰን ሃጅ አሊ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመላ ሃገሪቱ መነሳሳቱ እየበረታ በመጣበት በዚህ ጊዜ የመንግሥቱ መሪዎች መራራቅና መናቆራቸውን አስወገደው በሚያግባቧቸው ነጥቦች ላይ እንዲሠሩ፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክም በካቢኔያቸው ውስጥ ሹም ሽር ወይም ሽግሽግ እንዲያደርጉና አዳዲስ ሰዎችን እንዲያስገቡ መክረዋል።

ጊዜያዊው መንግሥት የሃገሪቱ ህግ አውጭ ምክር ቤት የሚቋቋምበትንና በአውሮፓ የዘመን አቆጣጠር ለ2023 ዓ.ም. መጨረሻ አካባቢ /የዛሬ ሁለት ዓመት መሆኑ ነው/ የታቀደው አጠቃላይ ምርጫ የሚካሄድበትን የጊዜ ሰሌዳ እንዲያወጣም አሊ አሳስበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዶክ በቴሌቪዥን ቀርበው “መንግሥታቸው ለመደራደርና ማንኛውንም የፖለቲካ ውዝግብ በንግግር ለመፍታት ቁርጠኛ መሆኑንና የሰላማዊ ሰልፈኞቹን ደኅንነት እንደሚያስጠብቁ” ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG