ዋሺንግተን ዲሲ —
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የሸቅጥና ምርት ስርጭት ሰንሰለት ማነቆዎች በሚፈቱበት መንገድ ላይ ከአንዳንድ የትላልቅ የችርቻሮ ምርት አቅራቢዎች፣ አከፋፋዮችና የወደብ ሠራተኞች ማህበራት ጋር ዛሬ ረቡዕ ተገናኝተው ይመክራሉ፡፡
በርካታ የንግድ ድርጅቶች በኮቭድ 19 ወረርሽኝ የተነሳ የሚያስፈልጓቸውን እቃዎች፣ የተጠናቀቁ ምርቶች ማግኘት እንዲሁም የሠራተኛ እጥረት የገጠማቸው በመሆኑ እየጨመረ የመጣውን የደንበኞች ፍላጎት ማርካት አለመቻላቸው ተመልክቷል፡፡
ከፕሬዚዳንቱ ጋር በዋይት ሀውስ ከሚገኙ የንግድ ድርጅቶች መካከል፣ ሆም ዲፖ፣ ዎልማርት፣ ዩፔኤስና፣ የሎስ አንጀለስ ዓለም አቀፍ የወደብና የመጋዘን ማህበራት ህብረት እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡