በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በኮቪድ-19 ክትባት ጉዳይ ለመወያየት ወደቺካጎ ይጓዛሉ


ፕሬዚደንት ጆ ባይደን
ፕሬዚደንት ጆ ባይደን

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ አሜሪካውያን የኮቪድ-19 ክትባት መከተብ ግዴታ ያደረገው መርሃ ግብራቸውን እርምጃ በተመለከተ ለመወያየት ዛሬ ወደቺካጎ ይጓዛሉ።

የዋይት ሃውስ የኮሮናቫይረስ ምላስ አስተባባሪ ጄፍ ዜንትስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ፕሬዚዳንቱ ከመቶ በላይ ሰራተኞ ያላቸው ኩባኒያዎች ክትባቱን መውሰድ አለዚያ በየሳምንቱ መመርመርን ግዴታ እንዲያደርጉ የሰጡት መመሪያ ምን ስኬት እንዳመጣ በቺካጎ ቆይታቸው ይመለከቱታል። የፕሬዚደንቱ መመሪያ ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ሰራተኞችን ወይም ከጠቅላላው የሀገሪቱ የሰራተኛ ሃይል ሁለት ሦስተኛውን ይመለከታል።

ቺካጎ የዩናይትድ አየር መንገድ መቀመጫ ስትሆን አየር መንገዱ የፕሬዚዳንቱን የክትባት ግዴታ ትዕዛዝ መጀመሪያ ተግባራዊ ካደረጉ አየር መንገዶች አንዱ ነው። ዩናይትድ ስድሳ ሰባት ሺህ ሰራተኞቹ በሙሉ እንዲከተቡ ያዘዘ ሲሆን በማስከተልም አሜሪካን አየር መንግድ እና ሊሎችም ይህንኑ አድርገዋል።

የፕሬዚዳንት ባየደን ሰራተኞች እንዲከተቡ የማይከተቡት ደግሞ በየሳምንቱ እንዲመረመሩ የሚያዘውም መመሪያ የፊዴራል መንግሥቱን ቁዋሚና የኮንትራት ሰራተኞች በሙሉ ይጠቀልላል።

የባይደን አስተዳደር ቤት ውስጥ የሚደረግ ፈጣን የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ለማምረት አንድ ቢሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚመድብ የዋይት ሃውሱ የኮቪድ ምላስ አስተባባሪ አክለው ገልጸዋል።

XS
SM
MD
LG