በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ሀላፊዎች ከሀገር እንዲወጡ ማዘዟን አሜሪካ አወገዘች።


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

ኢትዮጵያ የተባበሩትመንግሥታት ድርጅት ሰባት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሃገር እንዲወጡ መወሰኗን ዩናይትድ ስቴትስ አውግዛለች። የኢትዮጵያ መንግስት በአስቸኳይ ውሳኔውን እንዲቀይርም ጥሪ አቅርባለች።በተመሳሳይ የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮጉተረዥ 'ኢትዮጵያ የድርጅቱ ኃላፊዎች በሀገር የውስጥ ጉዳዮች ጣልቃ ገብተዋል' በማለት ማባረርሯ እንዳስደነገጣቸው ገልፀው፣ ባለስልጣናቱ ስራቸውን መቀጠል በሚችሉባቸው መንገዶች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ሀላፊዎች ከሀገር እንዲወጡ ማዘዟን አሜሪካ አወገዘች።
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:01 0:00

(ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን የኢትዮጵያ መንግስትን ውሳኔ በመቃወምትላንት መግለጫ አውጥተዋል።

አንተኒ ብሊንከን መግለጫው ያወጡት የኢትዮጵያ መንግስት፤ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባላት መሀከል- የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ሀላፊ፣ የድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች የኢትዮጵያ ቢሮዎችኃላፊዎችና አንድ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ማስተባባበሪያ ቢሮ የቡድን ኃላፊን ጨምሮ -ሰባት የድርጅቱ ሠራተኞች በ72 ሰዓት ውስጥ ከሃገር እንዲወጡ ያለበትን ውሳኔውን ካስታወቀ በኋላ ነው።

አንተኒ ብሊንከን ባወጡት መግለጫ፣ ፕሬዝዳንት ባይደን በወሩ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትሁኔታ ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ማዕቀብ መጣል የሚያስችል ትዕዛዝ መፈረማቸውን አስታውሰው"ለኢትዮጵያ ህዝብ ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ በሚያደርጉ ላይ ይህንን ትዕዛዝም ሆነ ሌሎች መንገዶችን ተግባራዊ ለማድረግ አናመነታም" ሲሉ ተናግረዋል።

ሌሎች የዓለም አቀፉ ማህብረሰብ አባላትም በኢትዮጵያ መንግስት እና ሰብዓዊ እርዳታ እንዳይደርስ በሚያደርጉ አካላት ላይ ተመሳሳይ ግፊት እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።

ብሊንከን በመገለጫቸው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮውች ኃላፊ የሆኑትማርቲን ግሪፊትስ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ ረሃብ እየተጠቃች ነው ማለታቸውን ተከሎ ውሳኔው መተላለፉን ተናግረዋል። ውሳኔው የዓለም አቀፉ ህብረተሰብ የሲቪሊያኖችን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረትና በአሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ በሚሊየኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ህይወት አድር እርዳታ ለመስጠትየሚደረገውን ጥረት አደናቃፊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደውን ሰባቱን ባለሥልጣናት ከሃገር የማስወጣት እርምጃ አስመልክቶ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬሽ ትላንት ባወጡት መግለጫ “የመንግሥታቱድርጅት እንቅስቃሴዎች ሁሉ በሰብዓዊነት፣ ባለመወገን፣ በገለልተኛነትና በነፃነት አስኳል መርኆች የሚመሩናቸው” ብለዋል ዋና ፀሃፊው።

ጉቴሬሽ አክለው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ኢትዮጵያ ውስጥ ምግብን፣ መድኃኒት፣ ውኃ፣ የንፅህና መጠበቂያ አቅርቦቶችን ጨምሮ ህይወት አድን እርዳታ እጅግ ለሚስፈልጋቸው ሰዎች እያደረሰ መሆኑን ጠቁመው ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት የድርጅታቸው ሠራተኞች ይህንኑ እያከናወኑ ስለመሆናቸው ሙሉ መተማመን እንዳላቸው ገልፀዋል።

የኢትዮጵይ መንግስት ከሀገር እንዲወጡ የወሰነባቸው የእርዳታ ሰራተኞች በሀገር ውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባታቸውን ያስታወቀ ሲሆን ከሀገር ለመውጣት የ72 ሰዓታት ጊዜ ሰጥቷቸዋል።

ጉዳዩን አስመልክቶ የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በትዊተር ገፃቸው ባሰራጩት መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ሰባቱን ከፍተኛ የተባበሩት መንግስታት ባለስልጣናት ለማባረር የወሰነውንእርምጃ ተቃውመዋል። ውሳኔው መንግስት ለአለፉት 11 ወራት የሰብዓዊ ርዳታ እንዳይደርስ በማድረግዓለም አቀፉን የሰብዓዊ ርዳታና መብቶችን ህግጋት ሲጥስ መቆየቱን የሚያሳይ ነው ብለዋል። መግለጫውየኢትዮጵያ መንግስት ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀመበት ነው ሲል ከሶ ዓለም አቀፉ ማህብረሰብሰብዓዊ ቀውሱን ለማስቆም አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስድ ጠይቀዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ላለፉት 11 ወራት ሲካሄድበቆየው ግጭት የደረሰውን እንግልት፣ የውሲብ ጥቃት፣ ዝርፊያና ሰብዓዊ እርዳታ ሰጪ መኪናዎችእንዳይንቀሳቀሱ በማገድ ሲፈፀሙ የቆዩ የመብት ጥሰቶችን ሲመዘግቡ መቆየታቸውን ያስታወቁ ሲሆን ያሳለፍነው ሰኔ የአፍሪካ ህብረት በኢትዮጵያ እየተፈፀመ ያለውን የመብት ጥሰት የሚመረምር አጣሪ ኮሚቴማቋቋሙን ገልፆ ነበር።

በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ግጭት ከተነሳ አንስቶ የዩናይትድ ስቴትስመንግስት ለግጭቱ ሀላፊነት አለባቸው ባላቸውና ምግብ፣ ምግብና መድሃኒት ለሚያስፈልጋቸው እርዳታ እንዳይደርስ አግደዋልባላቸው ግለሰቦች ላይ ማዕቀብ እንደሚጥል አስታውቋል። የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ እንዲደርስ አለማገዱን በተደደጋሚ ቢያስታውቅም፣ የእርዳታ ድርጅቶች ግን መንግስት የበለጠ ጥረት ማድረግ እንዳለበት ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG