በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ሲጋራ አጫሾች በኮቪድ 19 የመሞት እድላቸው ከፍተኛ ነው" - አዲስ ጥናት


ፎቶ ፋይል፦
ፎቶ ፋይል፦

ከብሪታኒያ የወጣው አንድ አዲስ ጥናት ሲጋራ አጫሾች ከሌሎች በተለየ፣ በኮቪድ-19 ቫይረስ በጽኑ ሊታመሙ ወይም ሊሞቱ እንደሚችል አስታወቀ፡፡

ዩኬ ባዮባንክ የተባሉ የአጥኚዎች ቡድን በ420ሺ በጎ ፈቃደኞች ላይ እኤአ፣ ከጥር እስከ ነሀሴ 2020 ባደረጉት ጥናት፣ ከሆስፒታሎችና ጤና ጣቢያዎች ባገኟቸው መረጃዎችና በተመለከቷቸው የሟቾች ሰርትፊኬት፣ በሲጋራ አጫሾችና በቫይረሱ ሳቢያ በሚመጡ ህመሞች መካከል የጠነከረ ግንኙነት መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡

ትሮአክስ በተሰጠኘው የህክምና መጽሄት ላይ በታተመው ጥናት እንደተመለከተው በአሁን ወቅት ሲጋራ ከሚያጨሱት የኮቪድ ተጋላጮች ውስጥ 80 ከመቶ የሚሆኑት ወይ ሆስፒታል ይገባሉ ወይም ይሞታሉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳትን ጆ ባይደን ሶስተኛውን የማጠናከሪያ የኮቪድ 19 ከትባት ትናንት ሰኞ ወስደዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ክትባቱን የወሰዱት አስተዳደራቸው ሶስተኛው የፋይዘር ማጠናከሪያ ክትባት ለተወሰነው የህብረተሰብ ክፍል እንዲሰጥ ከወሰነ ጥቂት ቀናት በኋላ ነው፡፡

ባይደን በተከተቡበት ወቅት “ዋነኛውና አስፈላጊው ነገር ሌሎች ብዙ ሰዎች እንዲከተቡ ማድረግ ነው” ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG