በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ለውጥ” - በሀዋሳ


“ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ለውጥ” - በሀዋሳ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:35 0:00
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ኢንዳስትሪው በዓለም አቀፉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በአገሪቱ ውስጥ ባለው የፀጥታ ችግር ስብራት እንደገጠው የኢትዮጵያ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው አስታወቁ።
“አሁን ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋት አንድነት፣ ፍቅር እና መከባበር ነው” ያሉት ዶ/ር ሄሩት “ቱሪዝምን ካለነዚህ እሴቶች ማሰብ አይቻልም” ብለዋል።
የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ደስታ ለዳሞ በበኩላቸው “ከቱሪዝም የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ የተረጋጋ፣ ሰላማዊ እና ፀጥታ የሰፈነበት ከተማ እና አገር መፍጠር ያስፈልጋል” ሲሉ አመላክተዋል።
ባለሥልጣናቱ ይህንን የተናገሩት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ42ተኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ቀን “ቱሪዝም ለሁለንተናዊ ለውጥ” በሚል መር ቃል ለ34ተኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ ሲከበር ነው።
XS
SM
MD
LG