ዋሺንግተን ዲሲ —
የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዕርጉዝ ሴቶች ከክትባቱ የሚያገኙትን የተፈጥሮ መከላከያ ለጽንሳቸው ማስተላለፍ የሚችሉ መሆኑን አንድ አዲስ ጥናት አመለከተ።
ከመውለዳቸው በፊት የፋይዘር ወይም የሞደርና የኮቪድ ክትባት የተከተቡ ሰላሳ ስድስት ሴቶች የወለዷቸው ህጻናት በሙሉ የኮቪድ መከላከያው ያላቸው ሆነው መገኘታቸውን ጥናቱ አሳይቷል።
በአሜሪካ የስነ ተዋልዶ እና የማህጸን እንዲሁም የእናት እና ጽንስ ህክምና መጽሄት ላይ የወጣው ጥናት ነው ይህን ያመለከተው።
የኒው ዮርክ ዩኒቨርስቲ ግሮስማን የህክምና ትምህርት ቤት ተመራማሪዎች ጥናቱን ማካሄዳቸውን ነው ሪፖርቱ ጠቁሟል።