በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዓለም ዙሪያ እየተዛመተ ያለው ዴልታው የኮሮናቫይረስ ዝርያ


በአሁኑ ወቅት በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወሩ ካሉት አሳሳቢ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች ሁሉ በብዛት እየተዛመተ ያለው ዴልታ የተባለው በፍጥነት ተላላፊው ዝርያ መሆኑን የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም የጤና ድርጅት የኮቪድ-19 ቴክኒካዊ ጉዳዮች ኃላፊዋ ማሪያ ቫን ኼርኾቭ በሰጡት ቃል አልፋ፥ ቤታ እና ጋማ የሚባሉት የቫይረሱ ዝርያዎች እያንዳንዳቸው ከአንድ ከመቶ ባነሰ ደረጃ እየተዛመቱ መሆኑን በብዛት እየተስፋፋ ያለው ዴልታው ዝርያ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ አውስትሬሊያዋ ሁለተኛው ትልቋ ከተማ ሚልበርን ውስጥ ትናንት በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች በግንባታ ኢንዱስትሪው ላይ የተወሰደውን ከኮቪድ ጋር የተያያዘ ገደብ በመቃወም ሰልፍ አድርገዋል።

ኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደን የኮቪድ ቁጥጥር ትዕዛዞችን በሚጥሱ ላይ የሚጣለው የገንዘብ መቀጮ ከህዳር ውር ጀምሮ ከፍ እንደሚደረግ አስታውቀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ደግሞ የዋሽንግተን ስቴት አገረ ገዢ ጄይ ኢንስሊ በክፍለ ሀገሯ በዴልታ ቫይረስ የተነሳ በእጅጉ በጨመረው የህሙማን ቁጥር ሆስፒታሎች በመጨናነቃቸው የፌዴራሉ መንግሥት ዕገዛ ጠይቋል።

XS
SM
MD
LG