በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ኮቪድ 19 ዜናዎች


በዩናይትድ ስቴትስ አይዳሆ ክፍለ ግዛት የሚገኙ ሆስፒታሎች፣ በኮቪድ 19 ህሙማን እየሞሉ በመምጣታቸው፣ የክፍለ ግዛቱ የጤናና እንክብካቤ መምሪያ፣ ህሙማንን በየቦታው መደልደል መጀመሩን ዛሬ ሀሙስ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የጤና መምሪያው ኃላፊ ዴቭ ጄፕሰን ህሙማንን በየህክምና መስጫዎቹ መደልደሉ የሚቆመው፣ ብዙ ሰዎች እንዲከተቡ በማድረግ ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ፈንድ አይ ኤም ኤፍ፣ የዓለም ባንክና፣ የዓለም ጤና ድርጅት ዝቅተኛና መከካለኛ ገቢ ላላቸው አገሮች የኮቪድ-19 ክትባት አቅርቦትን በቅንጅት ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ከዋነኞቹ ከክትባት አምራች ኩባንያዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

የውይይቱም ግብ በየአገሩ የሚገኙ 40 ከመቶ የሚሆኑ ሰዎችን፣ እኤአ በ2022 አጋማሽ ላይ ደግሞ ቢያንስ ማስከተብ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG