በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት በቅርቡ የፈፀማቸው አሰቃቂ የመብት ጥስቶች ሊጣሩ ይገባል - ቢል ለኔ ስዩም


ቢል ለኔ ስዩም
ቢል ለኔ ስዩም

የተባበሩት መንግሥታት እና የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን የጋራ ምርመራ ህወሓት ባለፉት ሁለት ወራት በአማራ፣ አፋር እና ትግራይ ክልሎች በፈፀማቸው አሰቃቂ የመብት ጥስቶች ላይም ሊቀጥል እንደሚገባው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የፕሬስ ክፍል ሃላፊ ቢል ለኔ ስዩም ተናግረዋል።

ውጤቱ በጥቅምት መጨረሻ ይፋ እንደሚደረግ የሚጠበቀው የአሁኑ የጋራ ምርመራ የተናጥል የተኩስ አቁም እስከተደረገበት ጊዜ ተፈፀሙ በተባሉ ጥሰቶች ላይ ብቻ ማተኮሩን ሃላፊዋ አስታውሰዋል።

ይሄ ግን በተጠቀስት ክልሎች በተፈፀሙት ከፍተኛ የመብት ጥሰቶች ላይም መቀጠል እንደሚገባው የገለጹት ሃላፊዋ መንግሥት ይሄንን አቋሙን ማሳወቁንም አመልክተዋል።

ህወሓት በጋራ ምርመራው ላይ እምነት እንደሌለው በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወቃል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

ህወሓት በቅርቡ የፈፀማቸው አሰቃቂ የመብት ጥስቶች ሊጣሩ ይገባል - ቢል ለኔ ስዩም
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:54 0:00


XS
SM
MD
LG