በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍርድ ቤቱ የፍልስጤማውያን ደጋፊዎቹ ተቃውሞ ህገመንግሥታዊ ነው አለ


ፎቶ ፋይል፦ ውሳኔውን የሰጡት በዩናይትድ ስቴትስ የስድስተኛው ምድብ የይግባኝ ፍርድ ቤት ዳኛ ጄፍሪ ሱተን
ፎቶ ፋይል፦ ውሳኔውን የሰጡት በዩናይትድ ስቴትስ የስድስተኛው ምድብ የይግባኝ ፍርድ ቤት ዳኛ ጄፍሪ ሱተን

ዩናይትድ ስቴትስ ፌዴራል ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት በሚችገን ክፍለ ግዛት ውስጥ በሚገኝ የአይሁድ ምኩራብ ፊት ለፊት ፍልስጤማውያንን በመደገፍ የሚደረገው ተቃውሞ በህገ መንግሥቱ የመጀመሪያው ማሻሻያ አንቀጽ የተጠበቀ መብት ነው አለ፡፡

ፍርድ ቤቱ ሚችገን አን አርበር ውስጥ በሚገኘው የቤተ እስራኤል ማምለኪያ አቅራቢያ በሚደረገው ተቃውሞ ላይ ገደብ እንዲጥል ወይም እንዲከለክል የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርጎታል፡፡

ተቃውሞው የሚካሄደው እኤአ ከ2013 በየሳምንቱ ጀምሮ ሲሆን “የአይሁድ ሥልጣን ሙስና ነው” ፣ የፍልስጤማውያንን እልቂት ወይም ሆሎኮስት ይቁም” የሚሉና የመሳሰሉ መፈክሮችን ያነገቡ ተቃዋሚዎች ይገኙበታል፡፡

ከአይሁዶቹ እልቂት (ሆለኮስት) የተረፉን ጨምሮ ወደ ምኩራቡ የሚመጡ አማኞች በሁኔታው የመንፈስ መረበሽ እንዳሳደረባቸው ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG