በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአፍሪካ አዲስ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር መቀነሱ ተገለጸ


ማት ሺድሶ ሞኤቲ
ማት ሺድሶ ሞኤቲ

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ድሬክተር ዛሬ ሀሙስ በሰጡት መግለጫ በአፍሪካ አዲስ የኮቪድ-19 ተጋላጮች ቁጥር ባላፈው ሳምንት ውስጥ በ23 ከመቶ መቀነሱን አስታወቁ፡፡

ቁጥሩ ካሻቀበበት ካለፈው ሀምሌ ወር ጀምሮ ባላፉት ስምንት ሳምንታት በዚህ መጠን ሲቀንስ ይህ የመጀመሪያ ነው ብለዋል፡፡

የጤና ድርጅት ኃላፊው ማት ሺድሶ ሞኤቲ ይሁን እንጂ የወረርሽኝ መጠን መቀነሱ ጥሩ ቢሆንም አዲስ ዴልታ ቫይረስ ዝርያ ቁጥር መጨመሩ ችግሩን ያባባሰው ሲሆን የሦስተኛ ዙር የወረርሽኙ ሂደትም ከተገመተው በላይ ዘለግ ላለ ጊዜ እንዲቆይ እንደሚያደርገው ይጠበቃል ብለዋል፡፡

ኃላፊዋ ጨመረው አፍሪካ ወረርሽኙ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ 200ሺ ሰዎች የሞቱበትን አሳዛኙን የኮቪድ-19 ወቅት አሳልፋለች ብለዋል፡፡

የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠርና መለካለክ ማዕክል እንዳስታወቀው ደግሞ ከአሁግሪቱ ሙሉውን ክትባት የወሰዱት 3 ከመቶ ብቻ ናቸው፡፡

XS
SM
MD
LG