በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታሊባን የተቃውሚዎቹን ይዞታ ተቆጣጥሬያለሁ አለ

በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ የአገሪቱ ግዛት በተቃዋሚዎች ስር የነበረችውን የታንጅሺር ሸለቆን መቆጣጠሩን ታሊባን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ 
በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ የአገሪቱ ግዛት በተቃዋሚዎች ስር የነበረችውን የታንጅሺር ሸለቆን መቆጣጠሩን ታሊባን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡ 

በአፍጋኒስታን ሰሜናዊ የአገሪቱ ግዛት በተቃዋሚዎች ስር የነበረችውን የታንጅሺር ሸለቆን መቆጣጠሩን ታሊባን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ፡፡

የታሊባን ቃል አቀባይ ዛቢሁላ ሙሃጂድ ዛሬ ባወጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ይህ ድል በመላ አገሪቱ ያለው ጦርነት አብቆቶ ወደ ብልጽግና እና ወደ ነጻነት የመሸጋገርን ጎዳና ይከፍታል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ፣ በአህመድ ማሱድ የሚመሩት የተቀዋሚዎቹ ኃይል፣ ግን በፌስ ቡክ በሰጡት ምላሽ የታሊባንን መግለጫን አስተባብለዋል፡፡

“ታሊባን ፓንጃሺርን ተቆጣጥሬያለሁ ማለቱ ሀሰት ነው፣ የተቃዋሚው ኃይል አሁንም ሁሉንም የስትራቴጂክ ቦታዎች እንደተቆጣጠረ ነው” ሲሉም አስረድተዋል፡፡

በሌላም በኩል፣ የዋይት ኃውስ ከፍተኛ ባለስልጣናት ሃገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ አፍጋኒስታን ውስጥ ትታቸው የወጣችው ቀሪዎቹን አሜሪካዊያንን እንደምታስወጣ ቃል ገብተዋል፡፡

የሪፐብሊካን ፓርቲ ቁልፍ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ሕግ አውጪ ሮን ክሌን ለሲ ኤን ኤን የዜና ጣቢያ በሰጡት ቃል ግን ዩናይትድ ስቴትስ ለሁለት 10 ዓመታት አልቃይዳን እና ታሊባንን ስትዋጋ ከቆየችበት ከአፍጋኒስታን ከሳምንታት በፊት ብትወጣም, ወደ 100 የሚጠጉ አሜሪካዊያን በዛ እንዳሉ እንደሚያምኑ ተናግረዋል፡፡

“መውጣት እስከፈልጉ ድረስም እነሱን የምናወጣበት መንገድ እንፈልጋለን” ሲሉም ክሌን አክለው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ‘ዩናይትድ ሲቴትስ የአሜሪካ ወታደሮች ከታሊባኖች እንዲያመልጡ ያገዙ አፍጋኒስታኒያውን ማገዟን ትቀጥላለችም’ ሲሉ ህግ አውጭው አስገንዝበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG