በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስፔስ ጄኔሬሽን አድቫይዘሪ ካውንስል የአፍሪካ አስተባባሪ ሆኖ የተመረጠው ትንሳኤ አለማየሁ ማነው?


Tinsae Ali
Tinsae Ali

የሃያ ሶስት ዓመቱ ወጣት ትንሳኤ አለማየሁ አሊ በቅርቡ የስፔስ ጄኔሬሽን አድቫይዘሪ ካውንስል የአፍሪካ አስተባባሪ ሆኖ ተመርጧል፡፡ በተጨማሪም በአፍሪካ ሕዋ ኢንዱስትሪ አሥር ከ30 ዓመት በታች ያሉ ወጣቶች ተብሎም መሆን የቻለ ወጣት ነው፡፡

ትንሳኤ በመቀሌ ዩኒቨርስቲ የመካኒካል ኢንጅነሪንግ ተማሪ ሲሆን ወደ መካኒካለ ምህንድስና ዘርፍ የገባው በኢትዮጵያ የህዋ ምህንድስና ዘርፍ ስለሌለ ተቀራራቢ ነው ብሎ እንደሆነም ይናገራል፡፡

ኢትዮጵያዊ የሆነው የሕዋ ሳይንስ እውቀት መፈተሽ አለበት የሚለው ትንሳኤ አሁን ደግሞ በስፔስ ጄኔሬሽን ምክር ቤት ውስጥ መላውን አፍሪካን እና ኢትዮጵያን ወክሎ ተመርጧል፡፡ ይሄ የተሰጠኝ ሹመት አፍሪካዊያን የበለጠ በሕዋው ሳይንስ ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸው የሚረዳ ሲሆን ከዘርፉ በብዙ የራቁትን ኢትዮጵያዊያንም መረጃ እንዲያገኙ እና ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማገዝ ይረዳል ይላል፡፡

የተሰጠው ሃላፊነትም ከባድ እንደሆነ እና ብዙ መስራት እንደሚያሻውም አልሸሸገም፡፡ ትንሳኤ አሊ ከዚህ ቀደም ከጋቢና ቪኦኤ ጋር ቆይታ የነብረው ሲሆን የአሁን ሽልማቱን በተመለክተ ከአሚሪካ ድምጽ ጋር ያደረገው ቆይታ ከቀድሞ ቃለመጠይቁ ጋር ተጣምሮ ተሰናድቷል፡፡

XS
SM
MD
LG