በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሙሉ በሙሉ የተከተቡ ሦስት የመወሰኛ ም/ቤት ሴኔተሮች በኮሮናቫይረስ ተያዙ


ፎቶ ፋይል
ፎቶ ፋይል

በዩናይትድ ስቴትስ ሙሉ በሙሉ የኮቪድ-19 ክትባት የወሰዱ ሦስት የመወሰኛ ምክር ቤት ሴኔተሮች ኮሮናቫይረስ እንደያዛቸው ዛሬ አስታውቁ።

ሴኔተሮቹ የሚሲስፒው ሪፐብሊካን ሮጀር ዊከር፣ የኮሎራዶው ዲሞክራት ጃን ሂከንሉፐር እና ከሁለቱም ፓርቲ ያልሆኑት የሜይኑ ነጻው ሴነተር አንገስ ኪንግ ናቸው። ሦስቱም የዩናይትድ ስቴትስ ሴኔተሮች ክትባቱን መከተባችን በቫይረሱ ምክንያት በጽኑ እንዳንታመም ረድቶናል ብለው እንደሚተማመኑ አስታውቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኒው ዚላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጃሲንዳ አርደርን በሀገራቸው ባለፈው ረቡዕ የተገኘው እና ከየካቲት ወር ወዲህ የመጀመሪያ የሆነው በቫይረሱ የተያዘው ሰው የታያዘው በዴልታው ዝርያ መሆኑን አስታወቁ።

አርደን የግለሰቡን መያዝ ተከትሎ በመላ ሃገሪቱ የሦስት ቀን በትልቋ ኦክላንድ ከተማ እና ሰውየው ተጉዞ በነበረበት የባህር ዳር ከተማ ደግሞ ለአንድ ሳምንት የሚቆይ የእንቅስቃሴ ክልከላ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG