በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያ መንግሥት "አቅጣጫ ተሰጥቷል" ያለበትን መግለጫ አወጣ


የሀገር መከላከያ ሠራዊትን ጨምሮ ሌሎችም የጸጥታ ኃይሎች በህወሓት ኃይል ላይ እርምጃ እንዲወስዱ መንግሥት አቅጣጫ ማስቀመጡን ገለፀ።

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ “አሸባሪው ጁንታ” ብሎ ከገለጸው ከህወሓት “ሕዝቡ እስከ ዘለዓለሙ ካልተለያየ በቀር፣ ገበሬው ተረጋግቶ ማረስ እንደማይችል ግልጽ ሆኗል” ሲል አስታውቋል።

“ጁንታው እየከፈተ ያለው ጥቃት ሕዝባዊ መልክ እንዲይዝ በማድረግ ስለሆነ መመከት የሚገባውም በዚያ አግባብ ነው፤ የመላው ሕዝባችንን የማያዳግም ምላሽ ሊያገኝ ይገባል“ ሲልም ነው ጽ/ቤቱ በመግለጫው ያከለው።

“የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን፣ የክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች፣ ይህንን ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይልና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ ብርቱና የማያዳግም ክንዳችሁን እንድታሳርፉ አቅጣጫ ተቀምጦላችኋል“ ሲልም የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት መልዕክት አስተላልፏል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የኢትዮጵያ መንግሥት "አቅጣጫ ተሰጥቷል" ያለበትን መግለጫ አወጣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:04 0:00


XS
SM
MD
LG