በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሞዛምቢክ ታጣቂዎችን ለመዋጋት የደቡብ አፍሪካ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ላኩ


የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ኔይሲ
የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ኔይሲ

በሞዛምቢክ አስቸጓሪ ሁኔታ ውስጥ በምትገኘው ሰሜናዊ የካቦ ዴልጋዶ ከተማ ትላንት የተገኙት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ኔይሲ በአካባቢው የሚገኙ ታጣቂዎችን እንዲዋጉ የደቡብ አፍሪካ ልማት ማህበረሰብ (ሳዴክ) ወታደሮች መሰማራታቸውን አስታውቀዋል።

በተጠንቀቅ ላይ የሚገኙት ወታደሮችም ከአንጎላ፣ ቦትስዋና፣ ሌሶቶ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ታንዛኒያ የተውጣጡ መሆናቸው ተገልጿል። የሳዴክ ወታደሮች በቦታው እንዲገቡ የተደረገው የሞዛምቢክ እና ሩዋንዳ ጦር ለሁለት አመት በእስላማዊው ታጣቂ ቡድን ተይዞ የነበረውን ጦር ማስለቀቃቸው እሁድ እለት ካስታወቁ በኃላ ነው። ቻርልስ ማንግዊሮ ከማፑቶ ያደረሰንን ዘገባ፣ ስመኝሽ የቆየ ታቀርበዋለች።

የሞዛምቢክ ፕሬዚዳንት ፊሊፔ ኔይሲ በዳቦ ዴላጎ ዋና ከተማ ተገኝተው በመንግስት የቴሌቭዥንና ሬዲዮ ጣቢያዎች በቀጥታ ባስተላለፉት መልዕክት የደቡብ አፍሪካ ወታደሮች በአካባቢ የተሰማሩት ታጣቂዎችን ለመዋጋት መሆኑን ገልፀዋል።

ከአምስት የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡት ወታደሮች እያደረጉት ላሉት አስተዋፅኦ አመስግነው የእስላም ታጣቂዎቹን ለመዋጋት የቅንጅት ስራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በሞዛምቢክ ታጣቂዎችን ለመዋጋት የደቡብ አፍሪካ ሀገራት ወታደሮቻቸውን ላኩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:16 0:00


XS
SM
MD
LG