በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የዚህ ገጽ ዋና ዓላማ በትዳር ውስጥ አይወሩም የተባሉ ነገሮች እንዲወሩ ማድረግ ነው" ወ/ሮ ቲና ተረፈ


Tina Terefe Yeenatoch weg fb page founder

የእናቶች ወግ እና የልጆች አስተዳደግ የፌስቡክ ገጽ ከተመሰረተ አንድ ዓመት ሞላው ይሄ ገጽ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከ160 ሺ የሚጠጉ አባላት ሲኖሩት በቀን ከመቶ በላይ ፖስቶችን ያስተናግዳል በዚህ ገጽ ላይ አባል የሆኑ ሴቶች ከተለያየ የሕይወት ተሞክሮ የመጡ ሲሆኑ በገጹ ላይ፣ ስለልጆች ጤና፣ አመጋገብ እና አስተዳደግ፣ ስለ ትዳር፣ ባልትና፣ እርግዝና፣ ስለ ሴቶች ጤና የመሳሰሉ ጥያቄዎች እና ውይይቶች ይስተናገዱበታል፡፡

አንዳንዴም በገጹ ላይ ከተሳታፊዎች የሚነሱ ጥያቄዎች መባል የለባቸውም ሚስጥር ናቸው፣ ነውር ነው በሚል ያከራክራሉ፡፡ ይሁንና የገጹ መስራች ቲና ተረፈ የዚህ ገጽ ዋና ዓላማ ሴቶች በቤታቸው ያሉባቸውን ችግሮች ግልጽ አውጥተው የሚወያዩበት እና መፍትሄ የሚጠቋቆሙበት እንዲሁም በልባቸው የያዙዋቸው ችግሮች የእነሱ ብቻ እንዳልሆኑ የሚረዱበት ነው ትላለች፡፡

የገጹ መስራች ቲና ተረፈ ነዋሪነቷን በአሜሪካ ያደረገች የሁለት ልጆች እናት ስትሆን ከጊዜ በኋላ በአባቶች በቀረበ ጥያቄ መሰረት 'መልካም ቤተሰብ እና የልጆች አስተዳደግ' የሚል አባቶችም የታከሉበት ገጽም መስርታለች፡፡ከዚህ በተጨማሪም በትዳር ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመፍታት ሳምንታዊ የምክክር መርሃግብሮችንም እንደሚያዘጋጁ እና ለወደፊቱም ሰፋ ባለ መልኩ የመቀጠል ሃሳብ እንዳላቸውም አስታውቃለች፡፡

"የዚህ ገጽ ዋና ዓላማ በትዳር ውስጥ አይወሩም የተባሉ ነገሮች እንዲወሩ ማድረግ ነው" ወ/ሮ ቲና ተረፈ
please wait

No media source currently available

0:00 0:16:56 0:00


XS
SM
MD
LG