በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቲያትር 100ኛ ዓመት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሲዘከር


Sele theater Gondor University students
Sele theater Gondor University students

በኢትዮጵያ ዘመናዊ ቲያትር ከተጀመረ 100 ዓመት ቢሞላውም ነገር ግን በተጀመረበት ፍጥነት እየተጓዘ አይደለም ተቀዛቅዟል፤ ዘርፉ መነቃቃት አለበት ያሉ ባለሞያዎች ከጥቅምት 2013 ዓ.ም ጀምሮ ሲወያዩ ከርመው በየካቲት 2013 ስለቲያትር የተሰኘውን ቡድን በይፋ በመጀመር የተለያዩ መርሃግብሮችን እያዘጋጁ ይገኛሉ፡፡ ከሰሞኑም በጎንደር ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበባት ማዕከል ባዘጋጀው የሁለት ቀናት የውይይት መርሃግብር ላይ አጋሮች ነበሩ፡፡ ስለቲያትር ያገባኛል የሚሉ ሁሉ እንዲሳተፉበት የጎንደር ዩኒቨርስቲ ባዘጋጀው በዚህ መርሃግብር ላይ ውይይቶች፣ ጥናታዊ ጽሁፎች እና ካሊጉላ የተሰኘው በሮም ንጉስ ላይ የሚያጠነጥን አልበርት ካመስ የተጻፈ ዓለም አቀፍ ቲያትር አቅርበዋል፡፡

በመርሃግብሩ ላይ የወልቂጤ ዩኒቨርስቲ፣ ደብረማርቆስ እና የወሎ ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበብ ክፍሎችም የተሳተፉ ሲሆን፤ የኢትዮጵያ የዘመናዊ ቲያትር ጅማሮን አስታኮ በመላው ሃገሪቱ የቲያትር ጥበብ እንዲነቃቃ እና እንዲያድግ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ስለቲያትር ቡድን አባላትም በቦታው ተገኝተው ውይይቱን ተካፍለዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርስቲ የቲያትር ጥበባት ክፍል ሃላፊ የሆኑት አቶ አንተነህ ወርቅነህ ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ ቲያትር የተዳከመባቸውን ምክንያቶች ለማወቅ ቲያትር ሲጠነክር ምን እንደሚሆን መረዳት ያስፈልጋል የሚሉ ሲሆን የቲያትር ጥበባት ማዕከል የትምህርት ክፍሎች የተደራጁ መሆን አለባቸው ቲያትሮችም ዘመኑን የዋጁ እና ዘመናዊ ቲክኖሎጂን ያካተቱ መሆን ያሻቸዋል ይላሉ፡፡

ከእሳቸው ጋር እና በጎንደር ዩኒቨርስቲ የአራተኛ ዓመት የቲያትር ጥበባት እጩ ተመራቂ ተማሪዎች ከሆኑት ሙሉቀን ቢፍቱ እና ስንዱ ወንድሙ ጋር የነበረንን ቆይታ ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የቲያትር 100ኛ ዓመት በጎንደር ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሲዘከር
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:12 0:00



XS
SM
MD
LG