በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ


የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ እና የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ

ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ዕቃዎችን የጫኑ ረቡዕ እለት 40 የጭነት መኪኖች ከሰመራ ወደ መቀሌ መጓዝ መጀመራቸውን የኢትዮጵያ መንግሥት ገለጸ።

የ6 ቀናት የኢትዮጵያ ጉብኝታቸውን በትናንትናው ዕለት የጀመሩት አዲሱ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ፀሀፊ እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ወቅት ምክትል ጠ/ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ መንግሥት የአንድ ወገን ሰብዓዊ የተኩስ አቁም ቢያውጅም፣ ህወሓት ግን ህጻናት መሳሪያ እንዲታጠቁ እስከሚያደርግ ድረስ የኃይል እና የግጭት ተግባር ስለመቀጠሉ አብራርተው ኦቻ የህወሓትን ድርጊት እንዲያወግዝ አሳስበዋል፡፡

ከፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋርም የተወያዩት ሚስተር ግሪፊትስ በበኩላቸው በትግራይ ያለው የድጋፍ አቅርቦት መመናመን እንደሚያሳሰባቸው እና ተጨማሪ የአቅርቦት መስመሮች መኖር እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ከኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00


አስተያየቶችን ይዩ (2)

XS
SM
MD
LG