የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በቅርቡ ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በዓለም ዙሪያ 132 ሚሊየን የሚሆኑ ሴት ህፃናት ወደ ትምህርት ቤት አይሄዱም። ከቅርብ ግዜ ወዲህ ደግሞ በኮቪድ 19 ምክንያት የትምህርት አቅርቦት በመስተጓጎሉ 11 ሚሊዮን ሴት ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ላይመለሱ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ - ከነዚህ ውስጥ አብዛኞቹ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት የሚገኙ ናቸው።
ለዚህ መሰረታዊ ምክንያቱ ድህነት ቢሆንም፣ የፆታ እኩልነት አለመኖር፣ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃት፣ ያለ እድሜ ጋብቻና በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ግዜ ወዲህ በብዛት የሚስተዋለው ህገወጥ ስደት ለሴት ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጥ ምክንያት መሆኑን ከዚህ ቀደም ያነጋገርናቸው የትምህርት ባለሙያዎች ነግረውናል።
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የሆኑት ዶክተር ይልቃል ከፍያለ እንደገለፁልን በአሁኑ ሰዓት በክልሉ እንደ ያለ እድሜጋብቻ ከመሳሰሉት ባህላዊ ተፅእኖዎች በበለጠ - በቤተሰባቸው የኑሮ አቅም ምክንያት የመጣ የሴቶች ህፃናት ፍልሰት ለትምህርት ማቋረጣቸው ዋነኛ ምክንያት እየሆነ መትቷል።
በቤንሻንጉል ጉምዝ፣ በድባቅና ዳንጉር ወረዳዎች ከ25 አመታት በላይ በትምህርት ባለሙያነት ያገለገሉት አቶ ሙሉጌታ እድሜውገፍቶም እንዲሁ በስራ ላይ በቆዩባቸው አመታት በሴቶች ትምህርት ዙሪያ ያስተዋሏቸውን ችግሮች እንዲህያስረዳሉ።
ካምፌድ ወይም 'ትምህርት ለሴቶች ዘመቻ' የተሰኘው መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የተቋቋመው እነዚህን በመሰረታዊ ሁኔታ ከድህነት ጋር የተቆራኙና ሴቶችን ከትምህርት ገበታቸው የሚያርቁ ተግዳሮቶችን በመቅረፍ ሴቶችን ራሳቸውን እንዲችሉ ለማገዝ ነው። ድርጅቱ ላለፉት 18 አመታት በአምስት የአፍሪካ ሀገራት፣ በጋና፣ ማላዊ፣ ታንዛኒያ፣ ዛምቢያናዝምባብዌ ውስጥ እየሰራ ሲሆን ከ379 ሺህ በላይ ተማሪዎች በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል። ለመሆኑ በነዚህ ሀገራት የሴት ተማሪዎች ችግር ምን ያክል ተቀርፏል? ኢትዮጵያስ ከዚህ ምን ትማራለች?- በታንዛኒያ የካምፌድ ዳይሬክተር ሆነው ለሚያገለግሉት ሊዲያዊልበርት ያቀረብኩት ጥያቄ ነው።
"ችግሮችን ከስር መሰረቱ ለመፍታት በመቻላችን የሚማሩበት ሁኔታና የጀመሩትን ትምህርት የመቀጠሉ ሁኔታ ተሻሽሏል። ለምሳሌ በታንዛኒያ ስራ ስንጀምር 100 ሴት ተምሳሌቶች ነበሩን። አሁን ከሁለት ሺህ በላይ ሆነዋል። በአሁኑ ሰዓት በተለያየ ክፍለ ግዛት የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ 19 ሺህ ተማሪዎችም ድጋፍ እናደርጋለን።በአጠቃላይ ታኒዛኒያ ውስጥ እስከ ዛሬ ለ48 ሺህ ሴት ተማሪዎች ድጋፍ አድርገናል።"
ካምፌድ በታንዛኒያ በሰራባቸው አመታት ይህን ማድረግ የቻለው በተለይ ለሴቶች ከትምህርት ገበታ መራቅ ዋና ምክንያት የሆነውን ድህነት ለማስወገድ ከወላጆች፣ ከተማሪዎች፣ ከትምህርት ቤቶችና በቀጥታ ከማህበረሰቡ ጋርበመስራቱ መሆኑን ሊዲያ ዊልበርት ያስረዳሉ።
"ጥሩ ገቢ ያለው ቤተሰብ ልጆቹን ትምህርት ቤት አልክም ሲል አላየሁም። በርግጥ ሌሎች ችግሮች ሊኖሩ ይችላሉ ግን በድህነት ውስጥ እንደሚኖረው ሰው ሊሆን አይችም። ስለዚህ በዋናነት የምናደርገው ይህን የገንዘብ ችግር መቅረፍነው። በመንግስት ተቋማት በኩል ለትምህርት የሚሆናቸውን ወጪ መሸፈን የማይችሉትን ልጆች ለይተን በቀጥታ የገንዘብ ድጋፍ እናደርግላቸዋለን። ከዛ የትምህርት ቁሳቁስ፣ የትራንስፖርትና አንዳንዴም የሚኖሩበትን ቦታ እናመቻቻለን። ልክ ልጁን ወደ ትምህርት ቤት የሚልክ ወላጅ የሚያደርገውን እናደርጋለን።"
ካምፌድ በድርጅቱ ድጋፍ ተደርጎላቸው ለቁምነገር በበቁ አባላቱ አማካኝነት የተቋቋመ 'ለርነርስ ጋይድ' ወይም 'ተምሳሌት' የተሰኘ ፕሮግራምም አለው። ፕሮግራሙ በዋናነት አላማው የነበረባትን ችግር አሸንፋ፣ ተምራ ለቁም ነገር የበቃች ሴትለሌሎች ሴት ህፃናትና አቻዎቿ ምሳሌ እንድትሆን ማድረግ ነው።
ካምፌድ በሚንቀሳቀስባቸው አምስት አገራት ከ4000 በላይ ተምሳሌቶችን አፍርቷል። ከነዚህ አንዷ በታንዛኒያ ገጠራማአካባቢ ተወልዳ ወላጆቿን በልጅነቷ በማጣቷ ለችግር የተዳረገች፣ ሆኖም ካምፌድ ባድረገላት ድጋፍ ታግዛ ትምህርቷንበዩንቨርስቲ መጨረስ የቻለችው ዲያሪስ ማርቲን አንዷ ናት።
"ካምፌድ ባይረዳኝ ኖሮ ትምህርቴን መጨረስ አልችልም ነበር። ምናልባትም እንደ ታናናሾቼ ጎዳና ላይ እወድቅ ነበር።እነሱ ለተወሰነ ግዜ ጎዳና ወጥተው ነበር። ግን ካምፌድ ህልሜን እንዳሳካ እረድቶኛል። በተለይ ሌሎች እንደኔ ያሉትን፣እንደኔ ይቸገሩ የነበሩትን መርዳት እንድችል ረድቶኛል። የሁልግዜ ምኞቴ ዩንቨርስቲ ገብቼ ስጨርስ ሌሎች ሴትወጣቶችንና ረጂ የሌላቸውን ህልማቸውን እንዲያሳኩ መርዳት ነበር።"
ዲያሪስ አሁን በካፌድ ውስጥ ዋና ፕሮግራም ሀላፊ ሆና ትሰራለች። ለሌሎች ሴቶች ተምሳሌት በመሆን የፅናትንውጤት ታጋራለች፣ የስኬት መንገዷን ታሳያለች። የአቅም ችግር ያለባቸውን ደግሞ በድርጅቷ አማካኝነት እርዳታእንዲያገኙ ታግዛለች።
እንደ ሊዲያ ያሉ ሴቶችን ማስተማር ቤተሰብን፣ ማህበረሰብን፣ ብሎም ሀገርን ማስተማር ነው የሚሉት ሊዲያ የሴት ልጅመማር ለዓለም እድገት ወሳኝ መሆኑን ያሰምሩበታል።
"የተለያየ ባህል እና የኢኮኖሚ አቅም ማጣት ሴት ልጆች ድምፅ እንዳይኖራቸው ያደርጋል። ትልቅ ህመም ውስጥ ሆነውእንኳን ሀሳባቸውን በሙሉ ልብ ለመግለፅ ሊቸገሩ ይችላሉ። ስለዚህ ሴትን ልጅ ትምህርት ማስተማር የማህበረሰብንድምፅ መመለስ ማለት ነው።"
ካምፌድ ፕሮግራሙን በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የማስፋፋት እና ስኬታማ በአፍሪካ የሴት አስተማሪዎችን፣ የህግባለሙያዎችን፣ የንግድ ባለቤቶችን፣ የጤና ባለሙያዎችንና የመንግስት ሀላፊዎችን ቁጥር የማሳደግ እቅድ አለው።ያንን ለማሳካት እንደ ዲያሪስ ያሉ ተምሳሌቶች ሴቶች ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጎሉ ሌት ተቀን ይተጋሉ።