በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ሃላፊ ጉብኝት በኢትዮጵያ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸኃፊ እና የአጣዳፊ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸኃፊ እና የአጣዳፊ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸኃፊ እና የአጣዳፊ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፊትስ ዛሬ በኢትዮጵያ ለስድስት ቀናት የሚቆይ ይፋ ጉብኝት ጀምረዋል። ሚስተር ግሪፊትስ ጉብኝታቸውን አስመልክተው፣

"በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ኃላፊነቴ መደበኛ ተልዕኮዬን በኢትዮጵያ መጀመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። በሀገሪቱ በትግራይ እና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች ባሉት የትጥቅ ግጭቶች በአፋር፣ በሶማሌ፣ በደቡብ ክልሎች ባሉ የማኅበረሰቦች የእርስ በርስ ግጭቶች እና በሶማሌ በኦሮሚያ እና በአፋር ክልሎች ባለው ድርቅ የተነሳ በዚህ ዓመት በሀገሪቱ ያለው ሰብዓዊ ችግር ጨምሯል" ማለታቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ ያወጣው መግለጫ አውስቷል።

አስቀድሞም በጎርፍ መጥለቅለቅ፣ በአንበጣ መንጋ ወረራ፣ ስር በሰደደ የምግብ ዕጥረት እና በኮቪድ-19 ወረርሺኝ የተነሳ በነበሩባት ተግዳሮቶች ላይ እነዚህ ችግሮች ተጨምረውባታል ያሉት የዓለሙ ድርጅት ባለሥልጣኑ ባሁኑ ወቅት በሚሊዮኖች የተቆጠሩ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችዋ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።

ሚስተር ግሪፊትስ በጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት እንዲሁም ከሰብዓዊ ረዳኤት ተቋማት እና ከለጋሽ ማኅበረበሰብ ተወካዮች ጋር እንደሚነጋገሩ መግለጫው አመልክቷል።

በግጭቱ የተነሳ ለችግር ከተጋለጡ ነዋሪዎች ከራሳቸው ለመስማት እንዲሁም የሰብዓዊ ረድኤት ሰራተኞች ያሉባቸውን ተግዳሮቶች በአካል ተገኝተው ለመመልከት ወደትግራይ ክልል እንደሚጓዙ በባህር ዳር ከተማ ተገኝተው ከአማራ ክልል ባለሥልጣናት ጋር ለመወያየት ዕቅድ ያላቸው መሆኑን መግለጫው ዘርዝሯል።

"የሰባዓዊ ረድዔት ማኅበረሰቡ ላሉት ቀውሶች ምላሽ ለመስጠት ከኢትዮጵያ መንግሥት እና ህዝብ ጋር አብሮ በቁርጠኝነት ይሰራል፤ ይህ ጉብኝቴም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና አጋሮቹ የኢትዮጵያን ህዝብ በሚገባ መርዳት ስለሚችሉበት መንገድ ከሃገሪቱ መንግሥት እና ከአጋሮች ጋር ለመወያየት ዕድል ይሰጠናል ማለታቸውን የወጣው መግለጫ ጠቅሷል።

XS
SM
MD
LG