ዋሽንግተን ዲሲ —
ኦቲዝምና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ስላሉባቸው ህፃናት ያለው ግንዛቤ አሁንም አናሳ መሆኑን ተከትሎ ማህብረሰቡን ግንዛቤ ከማስጨበጥ አንስቶ ወላጆች እነዚህ አይነት እክሎች ያሉባቸውን ልጆች እንዴ መርዳት ይችላሉ በሚል ሀሳብ ዙሪያ ጠለቅ ያለ እውቀት የሚያስጨብጥ መፅሃፍ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር ውስጥ ቋንቋ ታትሞ ገበያ ላይ ውሏል። ይህን 'ሁሉም በአንድ' የተሰኘ መፅሃፍ የፃፈችው የአይምሮ ህክምና ባለሙያና መምህር የሆነችው መአዛ መንክር ስትሆን ስመኝሽ የቆየ ኦቲዝም ያለባቸውን ልጆች ለውጤት ማብቃት በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ አነጋግራታለች፣ ቀጥሎ ይቀርባል።
(ዝርዝሩን ከታች ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ)