በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢድ- አል አደሃ (አረፋ) በዓል አከባበር


1ሺህ 442ኛው የኢድ-አል አደሃ (አረፋ) በዓል አከባበርን በተመለከተ ከአዲስ አበባ፣ ከሃዋሳ፣ ከአምቦና ከዋሽንግተን ዲሲ ዘገባዎችን አጠናቅረናል።

በአዲስ አበባ

1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል ዛሬ በኢትዮጵያ በተለያዩ ሥነስርአቶች ተከብሯል ። በአዲስ አበባ ስታዲየም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች; የሃይማኖት አባቶች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት በከፍተኛ ድምቀት ተከብሯል::

በሥነ ስርዓቱ ላይ መልክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሀጅ ዑመር እድሪስ አረፋ የመተሳሰብ ; የአንድነት እና የአብሮነት በዓል ነው ብለዋል::

በሃዋሳ

የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል በተደረገው ገደብ አደባባይ ላይ ሳይከበር የቆየው በዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በሃዋሳ ከተማ መስቀል በአደባባይ ማክበራቸውን የእምነቱ ተከታዮች ተናግረዋል።። የሃዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ሪፖርት ልኳል።

በአምቦ

አምቦ የሚገኘው ዘጋቢያችን ናኮር መልካ በአንድ ቤተሰብ ቤት በመገኘት የ1442ኛ የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በኣል አከባበርን ታድሟል::የቤተሰቡ አባላትና ጎረቤቶች "በአሉ ሲከበር የሌላቸውን በመርዳት መሆን ይገባዋል" ሲሉ አሳስበዋል::

በዋሽንግተን

በኮቪድ 19 ቫይረስ ስርጭት ምክንያት ባለፈው ዓመት ሰብሰብ ብለው በዓልን ለማክበር ያልቻሉ የዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የእስልምና ዕምነት ተከታዮች ዘንድሮ ግን ተሳክቶላቸዋል። ዛሬ ረፋዱ ላይ በሪክ ሮክ መናፈሻ የተገናኙት ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በዓሉን በሚያከብሩበት አፍታ ስለ ሀገራቸው መልካም መልካሙን እንደሚመኙ፣ የተቸገሩትንም እንደሚያስቡ ተናግረዋል።

(ሁሉንም ዘገባዎች ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

የኢድ- አል አደሃ (አረፋ) በዓል አከባበር
please wait

No media source currently available

0:00 0:21:55 0:00


XS
SM
MD
LG