በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጄኮብ ዙማ የሙስና ወንጀል ክስ ሂደት ተላለፈ


የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ትናንት ከእስር ቤቱ በኢንተርኔት በቪዲዮ አማካይነት ችሎቱ ፊት ሲቀርቡ ከስክሪን ላይ የተወሰደ።
የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ትናንት ከእስር ቤቱ በኢንተርኔት በቪዲዮ አማካይነት ችሎቱ ፊት ሲቀርቡ ከስክሪን ላይ የተወሰደ።

በቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ ላይ የተመሰረቱት የሙስና ወንጀሎች ክስ ሂደት ለሚቀጥለው ነሐሴ ወር ተቀጥሯል።

የቀድሞ መኖሪያቸው ክዋዙሉ ናታል ክፍለ ግዛት ፒየተርማሪት ዝበርግ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ የክስ ሂደቱን እ. አ. አ ለነሃሴ 10 ቀጥረዋል። የጄኮብ ዙማ ጠበቆች የቀድሞው ፕሬዚደንት በአካል ችሎቱ ፊት ለመቅረብ ጊዜ እንዲኖራቸው እና በአግባቡ እንድንመክርበት ሂደቱ ይዛወርልን ብለው ስለጠየቁ ነው።

የ79 ዓመቱ ዙማ ከሁለት ሳምንታት ገደማ በፊት እጃቸውን ሰጥተው በሕገ መንግሥታዊ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበር በተበየነባቸው የዐስራ አምስት ወር እስራት ቅጣት ታስረዋል። ትናንት ከእስር ቤቱ በኢንተርኔት በቪዲዮ አማካይነት ችሎቱ ፊት ቀርበዋል።

እ.አ.አ በ1999 ዓመተ ምህረት ምክትል ፕሬዚደንት ሳሉ ከፈረንሳዩ ግዙፍ የመከላከያ ኩባኒያ ታሌስ ግሩፕ ጋር ሃገራቸው የመሳሪያ ግዢ ውል ስትዋዋል በርከት ያሉ የሙስና የማጭበርበር እና ሌሎችም ህገ ወጥ ተግባራት ፈጽመዋል ተብለው ተከሥሰዋል። ኩባኒያውም በማጭበርበር እና በህገ ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ በህጋዊ አካል ልባስ የማዘዋወር ወንጀል ተከሱዋል።

የቀድሞው ፕሬዚደንት መታሰራቸው በክዋዙሉ ናታል ክፍለ ሀገር ያስነሳው ተቃውሞ ወደ ኢኮኖሚ መዲናዋ ወደ ጆሃንስበር ተዛምቶ በተፈጠረ ሁከት፥ዝርፊያ እና ቃጠሎ ከሁለት መቶ በላይ ሰዎች መደላቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG