በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲስ ስታንዳርድ በጊዜያዊነት ታገደ


የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በኢንተርኔት ላይ ሚድያነት የተመዘገበውን አዲስ ስታንዳርድን ማገዱን አስታወቀ።

ባለሥልጣኑ ዛሬ ባወጣው ማሳሰቢያ ግንቦት 20/2013 ዓ.ም. የተመዘገበውን አዲስ ስታንዳርድን በጊዜያዊነት ያገደበትን ምክንያት ሲናገር “በደረሱት ቅሬታዎችና እራሱም ባደረገው ክትትል አሳሳቢ አካሄድ በማስተዋሉ” መሆኑን ገልጿል።

“ሚድያው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተላለፈ ውሣኔን ባለማክበር አንድን የሽብር ቡድን “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በደረሰ ሁኔታ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ መሆኑን አውቀናል” ይላል የባለሥልጣኑ ማስታወሻ። በመቀጠልም “እነዚህና ሌሎችም ተያያዥ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ጥልቅ ምርመራ ይደረግባቸዋል፤ ሌሎች እርምጃዎችም ይወሰዳሉ” ብሏል።

“የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለፕሬስ ነፃነትና ሙያዊና በሥነ ምግባር የሚገዛ ጋዜጠኛነትን ለማበረታታት ያለውን ቁርጠኛነት በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ” በገለፀበት በዚሁ መግለጫው “ነፃነት የሚመጣው ከኃላፊነትና ከተጠያቂነት ጋር መሆኑንም በተቆጣጣሪ አካልነቱ አጉልቶ ማስገንዘብ እንደሚፈልግ” አመክልቷል።

ሁሉም መገናኛ ብዙኃን የህግ የበላይነትን እንዲያከብሩና በኃላፊነት ስሜት እንዲሠሩ አሳስቧል።

XS
SM
MD
LG