በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይ ጥቃት በመድረስ ላይ እንደሚገኝ ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታወቀ


ሕፀፅ መጠለያ ካምፕ
ሕፀፅ መጠለያ ካምፕ

በትግራይ ክልል በሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ላይ ጥቃት በመድረስ ላይ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ አስታወቀ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ለቪኦኤ ገለጻ ያደረጉት የኤጄንሲው የኮሙኒኬሽን እና የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር በአካል ንጉሴ፣ በክልሉ ከሚገኙ አራት የስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ሺመልባ እና ህጻጽ የተባሉ ሁለት ጣቢያዎች ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት በሕወሓት ጉዳት ደርሶባቸው ሲዘጉ ከተበተኑ ስደተኞች መካከል ከ9 ሺ በላይ የሚሆኑት ተሰብስበው ወደተቀሩት ሁለት ጣቢያዎች መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይሁን እንጂ አሁን ላይ ተበትነው በሚገኙ ስደተኞች ላይ ጥቃት በመፈጸም ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች መኖራቸውን እንዲሁም ከተከዜ ተሸግረው ማይጸብሪ አካባቢ በሚገኙት ሁለት ጣቢያዎች የሚገኙ ስደተኞችም ለችግር መጋለጣቸውን ተናግረዋል፡፡

ስደተኞቹ ያለባቸውን ስጋት እና ችግሮች ከመቅረፍ ጋር በተያያዘ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ጠይቀዋል፡፡ የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር በትግራይ ክልል የሚገኙ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ጉዳይ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው የገለጹ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከሕወሓት ወገን የተባለ ነገር የለም፡፡

(ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)


XS
SM
MD
LG