በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል ቃል አቀባይ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ እና ሚዲያ ወቀሱ


 የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

የኢትዮጵያ መንግሥት የወሰደውን የተናጠል ተኩስ የማቆም ስምምነት የጣሰው ሕወሓት በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ መፈፀሙን የተናገሩት የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ የክልሉ መንግሥት " የህልውና ዘመቻ" ብሎ በሰየመውና ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ዘመቻ ህወሃትን ወደ ነበረበት መመለስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

ማክሰኞ ዕለት ለአሜሪካ ድምፅ ቃለ ምልልስ የሰጡት የትግራይ ክልል መንግሥት አመራር አባልና የትግራይ ማዕከላዊ ኮማንድ ቃል አቀባይ መሆናቸውን የተናገሩት አቶ ጌታቸው ረዳ "የትግራይ እናቶች ዘመቻ" በሚል አዲስ ስያሜ በደቡብ እና ምዕራብ ትግራይ በጀመሩት አዲስ ዘመቻ ተወረዋል ያሏቸውን የትግራይ መሬቶች በማስመለስ ኮረም እና ኣላማጣ ከተሞች በቁጥጥሩ ስር ማስገባታቸውን መግለፃቸው ይታወሳል።

አቶ ግዛቸው ህወሃት በአንድ ወደገን የተደረገውን የተኩስ አቁም በመቀበል ለትግራይ ሕዝብ እፎታ በመስጠትና ራሱንም በመለወጥ ወደ ሰላም መመለስ ሲገባው በአማራ ሕዝብ ላይ ክተት ዐውጆባቸው እንደነበር አስታውሰው በዚህም ምክኒያት ከመከላከል ወደ ማጥቃት መሻገራቸውን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ህወሓት በኢትዮጵያ ላይ እያደሰ ነው ያሉትን በደል በተመለከተ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፍትሃዊ እና ሚዛናዊ አካሄድ እየተከተለ አይደለም ሲሉ ተችተዋል።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

“ህወሃትን ወደ ነበረበት መመለስ እየተቻለ ነው” - አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:15 0:00


XS
SM
MD
LG