በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“የትግራይ ሕዝብ፤ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ አያውቅም” ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል


የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል
የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል

"የትግራይን መሬትን ወረው የያዙ ኃይሎች በአስቸኳይ ይውጡ ካልሆነ ግን ባለፉት ስምንት ወራት እንዳደረግነው ሁሉ ታግለን መብታችንን እናስከብራለን" ሲሉ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ።

“የትግራይ ሕዝብ፤ ሕዝብን እንደ ሕዝብ ጠላት አድርጎ ፈርጆ አያውቅም” ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን “የትግራይ ሕዝብ ትላንት የአማራ ጠላት አልነበረም፣ ዛሬም የአማራ ጠላት አይደለም ነገም የአማራ ሕዝብ ጠላት አይሆንም” ብለዋል።

በተያያዘም የክልሉ መንግሥት ባወጣው መግለጫ፤ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የትግራይ ተወላጆች በግፍ እየተገደሉ፣ እየታሰሩ፣ ከሥራቸውም እየተባረሩ ንብረታቸውም እየተዘረፈ ነው ሲል ከሷል።

(የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ኬኔዲ አባተ፣ የመቀሌው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አጽብሐና የባህርዷሯ ዘጋቢያችን አስቴር ምስጋናውን ያጠናቀሩትን ሁሉንም ያካተተ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

please wait

No media source currently available

0:00 0:17:43 0:00


XS
SM
MD
LG