በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአማራ ክልል መንግሥት ወደ ማጥቃት መሸጋገሩን አስታወቀ


የአማራ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ
የአማራ ክልል ቃል አቀባይ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ

የአማራ ክልል መንግስት ህወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን መጠነ ሰፊ ወረራ ለመመከት ከመከልከል ወደ ማጥቃት መሸጋገሩን የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አስታውቋል።

ለሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነትና ለአርሶ አደሩ የእርሻ ጊዜ ሥራ ተብሎ የተደረገውን የተኩስ አቁም ስምምነት "ህወሃት ለጦርነት ጉሰማ አውሎታል" በማለት በዛሬ ዕለት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የተናገሩት ያሉት የአማራ ክልል መንግስት ኮምንኬሽን ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ ከዚህ በኋላ ከመከላከል ወደ ማጥቃት እንደሚሸጋገሩ ተናግረዋል።

ህወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ በከፈተው መጠነ ሰፊ ጥቃት በራያ ፣ አላማጣ፣ ኮረም እንዲሁም ወልቃይት ጠገዴና ማይፀብሪ ፤ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በኩል ደግሞ ፃግብጅ፣ ዛታ እና አበርገሌ አካባቢዎች ዳግም ወረራ ከፍቷል ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም ይህንን በህልውና ላይ ያነጣጠረ ጥቃት ዝም ብሎ መመልከት ስለማይችል ከዛሬ ጀምሮ ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሯል ብለዋል::

በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው ይህው ቡድን ለሀገር ብቻ ሳይሆን ለዓለም አቀፍ ስምምነቶችም ተገዥ አለመሆኑን አረጋግጧል ያሉት አቶ ግዛቸው ሴቶችን እና ሕጻናትን እንዲሁም "ካህናትና አዛውንቶችን ከፊት በማሰለፍ ለጦርነት እየማገደ ይገኛል " ብለዋል።

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ትላንት ባወጣው መግለጫም ህወሓት ከአማራ ክልል ጋር በሚያዋስኑት ሁሉም አቅጣጫዎች መጠነ ሰፊ ወረራና ጥቃት እየፈጸመ እንደሆነ በመግለፅ ወንጅሎ ነበር።

(የአዲስ አበባውን ዘጋቢያችንን ኬኔዲ አባተ፣ የመቀሌው ዘጋቢያችን ሙሉጌታ አጽብሐና የባህርዷሯ ዘጋቢያችን አስቴር ምስጋናውን ያጠናቀሩትን ሁሉንም ያካተተ ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)

please wait

No media source currently available

0:00 0:17:43 0:00


XS
SM
MD
LG