በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የተመድ የሰብዓዊ መብት ካውንስል በትግራይ የመብት ረገጣ ጉዳይ ውሳኔ ማሳለፍ አለበት" ሂዩማን ራይትስ ዋች 


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት በትግራይ ክልል ቀውስ ጉዳይ አጀንዳ ይዞ እንዲነጋገር ሂዩማን ራይትስ ዋች አሳሰበ።

በትግራይ ክልል ስለደረሱ ከባድ የመብት ረገጣዎች ሪፖርቶች መውጣታቸውን ቀጥለዋል ያለው የሰብዐዊ መብት ድርጅቱ ሂዩማን ራይትስ ዋች ጉባኤ ላይ ያለው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዐዊ መብት ኮሚስን ጉዳዩን አጀንዳ ይዞ መነጋገር አለበት ይህን ደግሞ በአስቸኩዋይ ሊያደርገው ይገባል ብሏል።

ትግራይ ውስጥ ተፈጽመዋል በተባሉት የሰብዐዊ መብት ረገጣዎች ዙሪያ ባሁኑ ወቅት በተ መ ዱ የሰብዐዊ መብት ከፍተኛ ኮምስነሩዋ ጨምሮ በአገር ውስጥ፥ በአህጉራዊ እና ዐለም አቀፋዊ ተቋማት የማጣራት ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ሂዩማን ራይትስ ዋች የተ መ ድ የሰብዐዊ መብት ከፍተኛ ኮምሽነር የምርመራቸውን ውጤት ለምክር ቢቱ ጉባዔ እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ ውሳኔ ካልተላለፈ በስተቀር ምክር ቤቱ በምርመራው ውጤት ላይ ሊነጋገር አይችልም ብሏል።

የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ህግ የምርመራዉ ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ለሰብዐዊ መብት ምክር ቤቱ አስታውቀው

የምርመራው ውጤት አሁን ባለበት ደረጃ ላይ ለመነጋገር የሚፈቅድ ውሳኔ ከተላለፈ ግን የሂደቱን ተዓማኒነት ይጎዳል ሲሉ አሳስበዋል።

ሂዩማን ራይትስ ዋች በበኩሉ አሁን ካለው የክልሉ የጸጥታ ሁኔታ እና የመገናኛ እና የተደራሽነት ገደቦች አኩዋያ ምክር ቤቱ ስላለው ተጨባጭ ሁኔታ ወቅታዊ ሪፖርቶችን ማግኘት እና የጭካኔ አድራጎቶች እንዳይቀጥሉ የመከላከል ሃላፊነቱ ለመወጣት እንዲችል የቀረበውን ውሳኔ ማጽደቅ ይኖርበታል ነው ያለው።

XS
SM
MD
LG