በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታይላንድ የሌሊት ሰዐት እላፊ አውጃለች

Locals wait in line overnight for free coronavirus testing at Wat Phra Si Mahathat temple in Bangkok, Thailand, Friday, July 9, 2021. Faced with rapidly rising numbers of new coronavirus infections and growing concern over the proliferation of the…

ታይላንድ በዋና ከተማዋ ባንኮክ እና ቢያንስ ስድስት አዋሳኝ ክፍለ ሀገርዋ የኮቪድ አስራ ዘጠኝ ስርጭት እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የሌሊት የሰዐት እላፊ አውጃለች።

የህዝብ ማጓጓዣዎች እና የንግድ መደብሮች የመሳሰሉት ከምግብ ቁሳቁስ ሱቆች እና ባንኮች መሰል አስፈላጊ ተቁዋማት በስተቀር ዝግ ይሆናሉ።

ሰዉ የግድ አስፈላጊ ለሆነ ጉዳይ ብቻ ከቤቱ እንዲወጣ ከዚያ ውጪ ስራውን ቤቱ ሆኖ እንዲሰራ ተጠይቋል። ከአምስት ሰው በላይ አብሮ መሰብሰብ ተከልክሏል።

ሶስተኛ ዙር የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ማዕበል የገጠማት ታይላንድ ባሁኑ ወቅት በየቀኑ 9276 አዲስ የቫይረሱ ተያዦች የሚመዘገቡ ሲሆን ዛሬ 72 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን ይፋ አድርጋለች።

ቪየትናምም በዋና ከተማዋ ሆቺ ሚን ሲቲ እየተባባሰ ያለውን የቫይረሱን ስርጭት ለመታገል ለቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት የእንቅስቃሴ ክልከላ አውጃለች።

ይህ በዚህ እንዳለ ፈረንሳይ ውስጥ በዋናነት የሚዛመተው ዴልታ የተባለው የኮሮና ዝርያ እንደሚሆን የሚጠበቅ መሆኑን የጤና ሚኒስትሩ ተናገሩ፥ ከትናንት ሃሙስ ወዲህ ለቫይረሱ ከተጋለጡ ሰዎች መካከል የያዛቸው ይህ በፍጥነት ተላላፊው የቫይረስ ዝርያ መሆኑን አመልክተዋል።

በሌላ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ ለሞልዶቫ በአንድ ጊዜ የሚሰጠውን የጆንሰን ኤንድ ጆንሰኑን 500 000 ክትባቶች መላኳን ዋይት ሃውስ አስታወቀ። ይህ ወደ ሞልዶቫ የተላከው የክትባት ድጋፍ ዩናይትድ ስቴትስ ወደአውሮፓ ልትልክ በዕቅድ ከያዘችው የስድሳ ሚሊዮን ክትባት ድጋፍ የመጀመሪያው መሆኑ ተገልጿል።

XS
SM
MD
LG