በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ወታደሮች ከአፍጋኒስታን መውጣታቸውን ተከትሎ የታሊባን ቡድን የበላይነት እያገኘ ነው


የአፍጋኒስታን ወታደሮች ሰኔ 6፣ 2021 በካቡል የደረሰ የመንገድ ዳር የቦምብ ፍንዳታ አካባቢ ለቀው ሲሄዱ
የአፍጋኒስታን ወታደሮች ሰኔ 6፣ 2021 በካቡል የደረሰ የመንገድ ዳር የቦምብ ፍንዳታ አካባቢ ለቀው ሲሄዱ

በአፍጋኒስታን የታሊባን ቡድን የበላይነት እያገኘ ባለበት በዚህ ወቅት ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍጋኒስታን ለምን መውጣት እንዳስፈለጋት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ትላንት አብራርተዋል። ዩናይትድስቴትስ ለሁለት አስርት አመታት ያካሄደችውን ጦርነት አቁማ ወታደሮቿን እስከ ነሐሴ መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ ለማስወጣት በሂደት ላይ ናት።

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች መውጣታቸውን ተከትሎ ዋና ከተማዋን ባጂስ የወረሩትን የታሊባን ወታደሮችን ለማስቆም የአፍጋኒስታን ወታደሮች ተታኩሰዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የአሜሪካ ወታደሮችና ተቋራጭ ሰራተኞች ባግራም ይተሰኘውን የአየር መቆጣጠሪያ ለቀው የሄዱት ባለፈው ሳምንት ነበር። ይህም እ.አ.አ በ2001 የተጀመረው የአሜሪካ ወታደራዊ ተልእኮ ማብቃያ ሆኗል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን የአሜሪካ ወታደሮች ለመውጣታቸው ማሳመኛ ያሉትን ምክንያት ሀሙስ እለት ሲያቀርቡ ይህን ነበር ያሉት።

"ላለፉት 20 አመታት ወደ ትሪሊየን የሚጠጋ ዶላር ለስልጠናና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአፍጋን ብሄራዊ ደህንነትና መከላከያ አባላትን ለማሰልጠን ካወጣን፣ 2448 አሜሪካኖች ከተገደሉ፣ 20 ሺህ 722 ከቆሰሉና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የአይምሮ ጤናቸውን ከሚያውክ እጅግ አሰቃቂ ገጠመኞች ጋር ከተመለሱ በኃላ የተለየ ውጤት የሚያስገኝ ምክንያት በሌለበት እንደገና ሌላ የአሜሪካ ትውልድ ለጦርነት ወደ አፍጋኒስታን አልክም።"

የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት እንደሚሉት ሙሉ ለሙሉ ከአፍጋኒስታን የመውጣቱ ሂደት በነሐሴ መጨረሻ ይጠናቀቃል። ባይደን በሚያዚያ ወር ላይ ውሳኔውን ሲያሳልፉ ዩናይትድ ስቴትስ እ.አ.አ በመስከረም 11፣ 2011 ዓ.ም በሀገሯ ላይ ጥቃት አድርሶ በነበረው የአል-ቃኢዳ ቡድን ዙሪያ ያለውን ስጋት ሙሉ ለሙሉ ማስወገዷን ገልፀው ነበር።

ሆኖም ታሊባን ቁልፍ የሆኑ ከተማዎችን በብዛት እየተቆጣጠረ መሆኑን ተከትሎ የአፍጋን መንግስት በቅርቡ ሊወድቅ ይችላል የሚለው ስጋት እያየለ ነው።

ባይደን በበኩላቸው ዩናይትድ ስቴትስ የአፍጋን ወታድሮችን መደገፏን እንደምትቀጥል፣ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደምታደርግና የሴቶችን መብት ለመከላከል እንደምስትሰራ ገልፀው የአፍጋን አመራሮች እራሳቸውን ማጠናከር ይገባቸዋል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG