አዲስ አበባ —
የኢትዮጵያ መንግስት የተናጥል ተኩስ አቁም በማወጅ መከላከያ ሰራዊትን ከትግራይ ማስወጣቱን መግለጹን ተከትሎ ክልሉን የተረከበውየትግራይ መከላከያ ኃይል በመባል የሚታወቀው በሕወሓት የሚመራው ኃይል የንጹኃን ግድያን ጨምሮ የተለያዩ ኢሰብዓዊ ድርጊቶችንበመፈጸም ላይ እንደሚገኝም የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው፡፡
የራያ ራዩማ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት እና የውጭ ግንኙነት ኃላፊ ጌታቸው ከበደ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ መከላከያሠራዊት ከትግራይ ክልል መውጣቱን ተከትሎ አሁን ላይ በሕወሓት ኃይል ቁጥጥር ስር በደቡባዊ ትግራይ በሚገኘው የራያ አዘቦ አካባቢየሚገኙ የራያ ተወላጆች ለበርካታ ችግሮች መጋለጣቸውን ገልጸዋል፡፡ እስካሁን 50 የሚደርሱ ንጹኃን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታመገደላቸውን እና ከ30 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውንም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል፡፡
የመከላከያ ሠራዊት ከክልሉ የወጣበትን ምክንያት የሚደግፉት፤ የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄምበበኩላቸው በክልሉ 22 አባሎቻቸው በሕወሓት ኃይል ተገድለዋል ብለዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ከሕወሓት አካል፣ መረጃ ለማግኘትየተደረገው ጥረት ለጊዜው ሊሳካ አልቻለም፡፡
(ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ)