በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጄከብ ዙማ እጃቸውን ሰጡ


ቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ 
ቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ 

የዐስራ አምስት ወራት እስራት ቅጣት የተፈረደባቸው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚደንት ጄከብ ዙማ ትናንት ሌሊት እጃቸውን ሰጥተዋል።

ዙማ እጃቸውን እንዲሰጡ ከተሰጣቸው የዕኩለ ሌሊት የጊዜ ገደብ ሳይደርስባቸው በጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብለው ለፖሊስ እጃቸውን የሰጡ ሲሆን ከመኖሪያ ቤታቸው በፖሊስ ታጅበው ወደ እስር ቤቱ ተወስደዋል።

ዙማ በፕሬዚደንትነታቸው ዘመን ፈጽመዋል በተባሉበት መጠነ ሰፊ የሙስና ወንጀል የቀረቡባቸውን ክሶች የሚመረምረው ኮሚሽን ፊት ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ የተሰጣቸውየፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባለማክበራቸው የደቡብ አፍሪካ ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ችሎት በመዳፈር ወንጀል የአንድዐመት ከሶስት ወር እስራት ቅጣት እንደፈረደባቸው ይታወሳል።

እስከትናንት ረቡዕ እኩለ ሌሊት ድረስ እጃቸውን የማይሰጡ ከሆነ እንዲታሰሩ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG